የኢፌዴሪ አየር ኃይል የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በግብርና ልማት ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 23 ቀን 2018 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት እና ከግብርና ሚኒስቴር የመጡ ከፍተኛ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በአየር ኃይል በግብርና ዘርፍ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተው፣ በቀጣይ በጋራ ለመስራትም ውይይት አድርገዋል።
የአየር ኃይል ወታደራዊ መደብሮችና መዝናኛ ክበቦች ኃላፊ ኮሎኔል ንጉሴ ለማ፣ አየር ኃይል ከመደበኛ የሀገር ደህንነት ተልዕኮው ጎን ለጎን በምግብ ራስን ለመቻልና የሠራዊቱን ኑሮ ለማሻሻል ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
በተቋሙ ውስጥ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተለያዩ የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ ሲሆን፣ በተለይም የእንስሳት ተዋፅኦ አቅርቦትን ለማስፋት ሰንጋና ፍየሎችን የማድለብ፣ የዶሮ እርባታና የወተት ላሞችን የማርባት ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።
በቀጣይም በቅርበት በመስራት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ንጉሴ ደቻሳ በበኩላቸው፣ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ከዋና ተልዕኮው ባሻገር በግብርና ልማት ላይ ሞዴል ሆኖ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
የአሳ ሀብት ልማት ዴስክ ኃላፊ ዶክተር ፋሲል ዳዊት በበኩላቸው፣ አየር ኃይል በተለያዩ የልማት ዘርፎች እያከናወነ ያለው ሥራ የሚደነቅ መሆኑን ጠቅሰው፣ በተለይም በዓሣ ሀብት ልማት ላይ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን በማሟላትና በቴክኒክ ድጋፍ በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።
በመጨረሻም፣ የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩትና የግብርና ሚኒስቴር ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ከአየር ኃይል ጋር በግብርና ምርምር፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በአቅም ግንባታና በተለያዩ የልማት ዘርፎች በጋራ ለመስራትና ተቋሙን ለመደገፍ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
ዘጋቢ እሱያውቃል ሙሉዬ
ፎቶ ግራፍ አረጋ ገሠሠ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
https://www.facebook.com/fdredefense.official
20
8August 29, 2026 4.3K