የ #Dheeራው ታሪካዊ “አብዮት" Dheeraa ላይ ከ54 ዓመታት በፊት አባቶቻችን የመጫና ቱለማ ማህበር… — Feyiso Kedir Law Office — TG.ME

"የ #Dheeራው ታሪካዊ “አብዮት"
Dheeraa ላይ ከ54 ዓመታት በፊት አባቶቻችን የመጫና ቱለማ ማህበር መስራቾች እንዲህ እንደ ዛሬ ህዝቡን ሰብስበው የኦሮሙማን አንድነት ለማጽናት መሰረት የጣሉበት የተቀደሰ ስፍራ ነው። ኦሮሞ ሙስሊምና ክርስቲያን እያለ በሀይማኖት እንዳይለያይ ከአንድ ማዕድ አብሮ ለክብረ በዓሉ የታረደውን የበሬ ስጋ እንዲመገቡ ተደረጎ የኦሮሙማን መንፈስ በማይናወጽ አለት ላይ መትከል ችሏል። . ግንቦት 1958 በአርሲ Dheeራ የመጫና ቱለማ መረዳጃ ማህበር ህዝባዊ ስብሰባ በጠራበት ሰአት ከጠቅላይ ግዛቱ በደረሰው መረጃ መሠረት የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ስብሰባው እንዳይደረግ አገደ፡፡ ኮሎኔል ሳህሌ ብሪ እንዳሉት፣ የደህንነት ክፍሉ ክልከላውን የለጠፈው በማህበሩ ቢሮ ነበር፡፡ ለአርሲ ጠቅላይ ግዛት ፖሊሲ ዋና አዛዥና ለፖሊስ ሠራዊት ጠቅላይ ጽሕፈት ቤትም፣ ስብሰባው እንዳይደረግ በኃይል ጭምር እንዲያስፈፅሙ ትዕዛዝ ሰጠ።
(ኦላና ዞጋ ግዝትና ግዞት 1985) . የክፍለ ሀገሩ እንደራሴ ደጃዝማች ሣህሉ ድፋዬም ለአዘጋጅ የአገር ሽማግሌዎች ዛቻ አዘል ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ሰጠ፡፡ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ፣ ቁጥር 541 ላይ “የሜጫ ቱላማ መረዳጃ ማኀበር ኢተያ ላይ ቅርንጫፍ እናቋቁማለን ብለው ነበር፡፡ ዓላማቸውን ብንጠይቅ ሕዝቡን መሰብሰብ ነው ስላሉን አልተቀበልናቸውም፡፡” በማለት ይፋ አደረገ፡፡ (ኦላና 1985) ኦላና ለመግለጫውም ሆነ ለፀጥታው መሥሪያ ቤት ክልከላ መንስኤው፣ እንደ ሰደድ እሳት በኦሮሞ አካባቢዎች የተቀጣጠለው እንቅስቃሴ ነው ይላል፡፡ አብዮቱ አሁን ግድ አለ የማህበሩ አመራር ክልከላውን ሲመለከት ለውይይት ቁጭ አለ፡፡ ብርቱ ውሳኔ፣ ወይ መገዛት ወይ እምቢኝ ማለት፤ ሌላ ምርጫ፣ ሌላ ማለዘቢያ የለም፡፡ ወሰነ፡፡ ከዚህ ጥሪ ፈርቶ መቅረት ማለት
(1)ለሌላ የተፈቀደ፣ ለኦሮሞ ሲሆን የተከለከለ ህገወጥነትን መደገፍ ነው (2) መተሳሰር ከጀመረው ኦሮሞ ጋር መቆራረጥ ነው የሚሉ ውሳኔዎችን .... በመሆኑም፣ ጥቅምት 5 ቀን 1959 ዓ.ል ብ/ጄኔራል ታደሰ ብሩ፣ብ/ጄኔራል ዳዊት አብዲ፣ ደጃዝማች ከበደ ብዙነሽ፣ ዶ/ር ሞጋ ፍሪሳ፣ አቶ በቀለ መኰንን፣ አቶ ተስፋዬ ደጋጋ፣ አቶ ገ/ስላሴ ወልዲያ፣ መ/አለቃ ማሞ መዘምር፣ አቶ ደጀኔ ቦጂኣ፣ አቶ ኤጄታ ፈይሳ፣ ወታደር ጨመዳ፣ ወታደር ኃይለማሪያም ዲማና ሌሎችም ከፊንፍኔ፣ በአቶ ዳዲ ፈይሳ የሚመራውም የአዳማ ቅርንጫፍ አንድ ላይ በመሆን dheራ ከተማ ገቡ፡፡ (ኦላና 1985) . ህዝቡም በበኩሉ፣ ቀደም ሲል ለሁለቱም ወገን ያልተቋረጠ ማስጠንቀቂያ ሲሰጥ የነበረውን ክፍል ከምንም አልቆጠረም፡፡ ለፍልሚያ ጭምር ተዘጋጅቶ ነበር፡፡ ለምሳሌ የአርሲ ቅርንጫፍ መስራች ሀጂ ሮበሌ ቱሬ
“… መብቱና ነፃነቱን ለማስከበር ልቡ ለተነሳሳ ሕዝብ ይቅርና፣ ለወዳጇ ልቧ የተነሳሳ አንዲት ሴት እንኳ፣ ወደ ኋላ አትመለስም” በማለት መቀስቀሱ ተመዝግቧል፡፡ . እውነትም በእለቱ ለፊንፍኔው ቡድን በብዙ ሺህ ወጥቶ ነው ደማቅ አቀባበል ያደረገላቸው፡፡ (ኦላና 1985) ጥንቃቄ ግን የሁለቱም ወገን ገንዘብ ነበረች፤ ከፊንፊኔ የሄዱት ጄኔራል ታደሰ ብሩንና ደጃዝማች ከበደ ብዙነሽን ብቻ በስብሰባው ላይ እንዲቆዩ በማድረግ ሌላው አካባቢውን እንዲቃኝ በጥበቃነት መደቡ፡፡ ከህዝቡ በኩልም፣ መሣሪያ ይዘው የመጡት በአቶ ዳዲ ፋይሳ መሪነት የጥበቃ ግዳጅ ተሰጥቷቸው ስብሰባው ማካሄድ ጀመረ፡፡ . በመሃል በጭላሎ አውራጃ ገዥ በደጃዝማች አስፋው ሺአምጥና በአውራጃው ፖሊስ ዋና አዛዥ በኰ/ል ልብሰቃል የተመራ የክልሉ አስተዳደር ተወካዮች ቡድን በስፍራው ደርሶ “ስብሰባው ሕገወጥ ነውና በትኑ!” የሚል ትእዛዝ ሰጠ፡፡ ተሰብሰቢው በበኩሉ እግዱ አገዛዙ በብሔር ማንነታቸው የተነሳ የሚያደርግባቸው አድልኦ እንጂ ረኃብ፣ በሽታና ድንቁርና የመዋጋት ዓላማ ይዞ የሚንቀሳቀስ ስብስብ ሕገ ወጥ ሊሆን እንደማይችል ባንድነት አሳወቁ፡፡ ይልቅስ በስብሰባው ላይ ሳይጋበዙ በመገኘታቸው ባስቸኳይ አከባቢውን እንዲለቁ አስገደዷቸው፡፡
ክርስቲያን፣ ሙስሊም፣ ወቄፈታ ሳይል በአስር ሺዎች የታደመ ኦሮሞ፣ በውይይቱ የደረሰባቸውን ኢኮኖሚያዊ ብዝበዛ እና ፖለቲካዊ ጭቆና ግልፅ አደረገ፡፡ የተቀናጀ እና አንድነት ያለው የመጀመሪያው የኦሮሞ ስብሰባ በመሆኑ የአንድነት ጥቅም በእጅጉ አስተዋለበት፡፡ ኦሮሞ ዳግመኛ ላለመለያየት ተማማለ፡፡ ሀጂ ስምቢሮ የተባለ ተሰብሳቢ፣ የኦሮሞ ሕዝብ አንድነት መቼም አስፈላጊ መሆኑን ሲያብራራ፣ “ትንንሽ ምንጮች ሲቀላቀሉ ወንዝ ይፈጥራሉ፤ አያሌ ወንዞችም ተደባልቀው ትልቅ ባህር ይሆናሉ፤ የኦሮሞ ህዝብም ብሄርና ሀገር የሚኖረው ሲሰባሰብ ነው” አለ፡፡
ሙስሊሞች፣ በክርስትያኖች የታረደ ዕርድ እንዲሁም ክርስቲያኖች በሙስሊሞች የታረደ ዕርድ ተመገቡ፡፡ ይህ እስከ ዛሬ ያልተሰማ ታሪክ በመሆኑ፣ ገዢ ልሂቁን የሚያስቆጣ ተጨማሪ መንስኤ ሆነ፤ ከሁሉ በላይ ደግሞ ማርካኪስ፣ “National and class conflict in the Horn of Afric ድርሳኑ ገፅ 260 ላይ እንደገለፀው ስብሰባው የተካሄደው በኢትዮጵያ እንዳይነገር በአዋጅ በታገደው አፋን ኦሮሞ መሆኑ፡፡ በቀጣይ የተካሄዱ ስብሰባዎችም በሙሉ፣ በአፋን ኦሮሞ ነበሩ፤ በዚያ መቆሚያ አልባ ጉልበቱ፣ ባለተሰጥኦው ወጣት መኮንን ማሞ መዘምር (መቶ አለቃ) የፃፋቸው ድራማዎች በስብሰባው ቀረቡ፣ አንደበተ-ርቱዕ ተናጋሪዎች በአፋን ኦሮሞ ንግግር አደረጉ፣ ድራማዎች፣ ግጥሞች እና የፀሎት ስነ- ሥርዓት ቀርበው፣ ተሰብሳቢውን በቁጭት እንባ አራጩ፤ በአገዛዙ ላይ እንዲነሳሱም ገፋፏቸው፡፡
የተደረገባቸውን ክልከላ እና እንደ ሁለተኛ ዜጋ መታየት፣ በግልፅ የተረዱበት እለት ነበር፡፡ነፃ መሆን እና ከሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦች እኩል የመታየት መብታቸውን ለማስከበር ቁርጠኝነታቸውን የገለጡበትም ነበር፡፡ አገዛዙ እንደፈለገው ሲበጫጭቃቸው እንዳልነበር፣ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ኦሮሞን በቀላሉ እርስ በርሱ የማጣላት እና የመከፋፈል አቅሙ ክፉኛ ተዳከመ፡፡ . ለዚህም ነው “የኦሮሞ ህዝብ ትግል የዱላ ቅብብሎሽ ትግል ነው” የምንለው፡፡ ትግሉን ትላንት ኦቦ ሌንጮ ወይም ዛሬ ጆዋር አይደለም የጀመሩት። በአያቶቻችን በንጉሱ ዘመን እነ አልይ ጭሪ፣ዋቆ ጉቱ፣ ጃራ አባገዳ አቀጣጥለውት ለነ ኮ/ል ዓለሙ ቂጤሳ፥ እነ ሃይለ ማርያም ገመዳ ፥እነ ጄኔራል ታደስ ብሩ እነ መቶ አለቃ ማሞ መዘምር…በወቅቱ በመቶ ሺዎች ኦሮሞዎችን ያንቀሳቀሱና ያነቁ ጀግኖቻችን ናቸው። ፡ የእነ ኦቦ ሌንጮ ትውልድና የመስረቱት ኦነግ የአባቶቻቸውን የትግል አደራ የተረከቡ ናቸው። Qubee Generation ይህ ትውልድ ከአያቶቹና ከአባቶቹ የተቀበለውን የትግል አደራ በልበ ሙሉነት የሚያሳካው ነው፡፡ ፡ የኦነግን መንፈስ ያሰረፁት ኦቦ ሌንጮ ለታና የእሳቸው ትውልድ እነሆ ለዛሬው የቁቤ ትውልድ በማስረከብ ቄሮ ከአባቶቹ የወረሰውን የአልገዛም ባይነት የፀረ ባርነት ትግሉን ሲያፋፍም አንዳንዶች ቁንጫ እንደበላው ውሻ እረፍት አጥተው ሕልምና ምኞታቸውን ወደ ቅዠት እየቀየረባቸው ክፉኛ የሚወግራቸው የበላይ የመሆን ጠኔ ፣ እውነት ኮቴዋን ባሰማች ቁጥር ለሚደነብሩ ደንባሮች እነሆ መልእክታችን፡፡ ፡ ….አትደንብሩ፡፡
🖕5💊4🤪3😁2🥴2👎1🤮1💩1🤡1🤣1👻1
September 6, 2026 885 3