እውቋ የአገረሰብ ሙዚቃ ንግሥት ዶሊ ፓርተን ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች ⚱️🙁😔 በአገረሰብ ሙዚቃ በዓለም… — 𝐅𝐢𝐧𝐟𝐢𝐧𝐧𝐞𝐞 𝐏𝐫𝐞𝐬𝐬 — TG.ME

🎁 እውቋ የአገረሰብ ሙዚቃ ንግሥት ዶሊ ፓርተን ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች ⚱️🙁😔

በአገረሰብ ሙዚቃ በዓለም ዙሪያ ከፍተኛ እውቅናን ያተረፈችው አንጋፋዋ አሜሪካዊት የሙዚቃ ደራሲ፣ አቀንቃኝ እና የፊልም ተዋናይ ዶሊ ፓርተን በ80 ዓመቷ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቷን ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል።

ዶሊ ፓርተን በ60 ዓመታት የሙዚቃ ሕይወቷ፣ በዓለም ዙሪያ በሚሊዮኖች ዘንድ የሚወደዱትን እንደ “ጆሊ”፣ “አይ ዊል ኦልዌይስ ላቭ ዩ”፣ “9 ቱ 5”፣ “ኮት ኦፍ መኒ ከለርስ” እና ሌሎች በርካታ የጥበብ ስራዎቿን አበርክታለች።

የዶሊን ሕልፈት ተከትሎ በርካታ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የሞያ አጋሮቿ እና አድናቂዎቿ ሀዘናቸውን በማህበራዊ ሚድያዎች ላይ እየገለጹ ሲሆን የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶላንድ ትራምፕ የአገሪቱ ባንዲራ ለአንድ ሳምንት ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ ማዘዛቸውን ሲኤንኤን ዘግቧል።

በዘመን አይሽሬ ስራዎቿ የ"ካንትሪ ሙዚቃ ንግሥት" የሚለውን የክብር ስም ያተረፈችው ዶሊ ፓርተን ከሙዚቃ ሕይወቷ ባሻገር በደግነቷ፣ በሰው ወዳድነቷ እና በሰብዓዊነት ተግባሮቿ ለብዙዎች አርዓያ በመሆኗ ትታወሳለች።

49 የስቱዲዮ አልበሞቿ እና ከ200 በላይ ነጠላ ዜማዎቿ በቢልቦርድ 'ሆት ካንትሪ ሶንግስ' ቻርት ላይ 25 ቁጥር አንድ ዘፈኖችን ያስገኙላት ሲሆን፣ ይህም በማንኛውም ሴት የካንትሪ ሙዚቃ አርቲስት ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል።

ዶሊ ፓርተን ባስደናቂ ስራዎቿ 11 የግራሚ ሽልማቶችን ያገኘች ሲሆን ከ20 በላይ በሚሆኑ ፊልሞች ላይም በተዋናይነት ተሳትፋለች።

ዘገበው የ[ መንግሥት ሚዲያ] ነው


ቴሌግራም፦
            📌t.me/Brics4ethiopia
Telegram
BRICS 𝐏𝐫𝐞𝐬𝐬
𝐁𝐑𝐈𝐂𝐒 𝐏𝐫𝐞𝐬𝐬 ____ 👉 | እኛ ገለልተኛ የሚዲያ ኩባንያ ነን 👉 | አለምአቀፍ ሰበር ዜናዎች እና 👉 | ጂኦፖለቲካ ፣ ደህንነትና የሚ/ትንተና 👉 | በ BRICS ቻናላችን ላይ ያገኛሉ ____ 👉 | Nuti miidiyaa walabaati. 👉 | ji’oopoolitikaa ፡nageenya fi 👉 | Xinxala miidiyaalee 👉 | "BRICS" n irraa...
❤2
August 26, 2026 792 1