ፑቲን ከቻይናው ፕሬዚደንት ጋር ተገናኙ!! በኪርጊዝስታን ቢሽኬክ እየተካሄደ ከሚገኘው የሻንጋይ የትብብር… — 𝐅𝐢𝐧𝐟𝐢𝐧𝐧𝐞𝐞 𝐏𝐫𝐞𝐬𝐬 — TG.ME

🇷🇺🇨🇳ፑቲን ከቻይናው ፕሬዚደንት ጋር ተገናኙ!!

በኪርጊዝስታን ቢሽኬክ እየተካሄደ ከሚገኘው የሻንጋይ የትብብር ድርጅት (SCO) ጉባኤ ጎን ለጎን የተገናኙት የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቪላዲሚር ፑቲን እና የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ፣ በየጊዜው እያደገ የመጣውን የሁለቱን ሀገራት ስትራቴጂካዊ ወታደራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አጋርነት ዳግም አረጋግጠዋል።

ፑቲን በኢኮኖሚ፣ በዲጂታል ቴክኖሎጂ እና በቪዛ ነፃ ዝውውር ዘርፎች ትብብራቸው በተሳካ ሁኔታ እየጎለበተ መሆኑን ሲገልጹ፣ ሺ ጂንፒንግ በበኩላቸው በአለም አቀፍ ደረጃ አለመረጋጋቶች ቢበዙም ቻይና ከሩሲያ ጋር በመሆን የምዕራባውያንን የበላይነት የሚፈታተን እና አዲስ ባለብዙ-ወገን የአለም ስርዓትን የሚገነባ ጠንካራ ግንኙነት እንደምትቀጥል አስታውቀዋል። የሕንድ እና የኢራን መሪዎችን ጨምሮ የሌሎች ቀጠናዊ ሀይሎች መገኘት የታየበት ይህ የቢሽኬክ ጉባኤ፣ የአለም አቀፍ የሀይል ሚዛን ከምዕራባውያን ወደ ምስራቅ እየተሸጋገረ መሆኑን የሚያሳይ ግልጽ መልእክት አስተላልፏል።


ቴሌግራም፦
            📌t.me/Brics4ethiopia
❤1
September 1, 2026 329