የ #አፍሪካ_ሕብረት በ #ሱዳን የሚካሄደውን የውይይት ጥረት መደገፉ በሲቪል ተቃዋሚዎች ዘንድ ብርቱ ተቃውሞ… — 𝐅𝐢𝐧𝐟𝐢𝐧𝐧𝐞𝐞 𝐏𝐫𝐞𝐬𝐬 — TG.ME

♦️ የ #አፍሪካ_ሕብረት በ #ሱዳን የሚካሄደውን የውይይት ጥረት መደገፉ በሲቪል ተቃዋሚዎች ዘንድ ብርቱ ተቃውሞ አስነሳ

የአፍሪካ ሕብረት ሰኞ ዕለት በሱዳን የተጀመረውን እና ሀገሪቱን ከእርስ በርስ ጦርነት ለማውጣት ያለመውን አዲስ የውይይት ጥረት እንደሚደግፍ አስታወቀ። ይሁን እንጃ የህብረቱን ውሳኔ የሲቪል እና የፖለቲካ ቡድኖች ወዲያውኑ ተቃውመውታል። ቡድኖቹ ጥረቱን በወታደራዊ ኃይሉ የሚመራ እና ግጭቱን ቅቡል ለማድረግ የተደረገ ሙከራ ነው ሲሉ ኮንነውታል።

በ #ካርቱም የሚገኙ እና በታዋቂ ግለሰቦች የተዋቀረው አዘጋጅ ኮሚቴ፣ በሠራዊቱ ከሚመራው መንግሥት በተሰጠ የደኅንነት ዋስትና መሠረት ከፖለቲካ እና ከሲቪል ማኅበራት አካላት ጋር ውይይቶችን ለማስተባበር እሑድ ዕለት ምክክር ጀምሯል።

የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን «በገለልተኛ የሱዳን የሀገር ሽማግሌዎች ኮሚቴ» የሚመራውን ውይይት እንደሚደግፍ ገልጾ፣ እርምጃው በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ በአውሮፓ ሕብረት፣ በኢጋድ እና በአረብ ሊግ በተዋቀረው የሕብረቱ የአምስትዮሽ አሠራር ሥር ያሉትን የዲፕሎማሲ ጥረቶች የሚያጠናክር ነው ብሏል።

ኅብረቱ ማንኛውም የፖለቲካ ሂደት፤ ሁሉንም ወገኖች ያካተተ መሆን እንዳለበት እና ቅቡልነት ባለቸው የሲቪል ተቋማት የምትመራ አንድነቷ እና ልዑላዊነቷ የተጠበቀ ሱዳንን ለመፍጠር ያለመ ሊሆን እንደሚገባው በድጋሚ አስታውቋል።

ሆኖም በአል-ዋቲክ አል-በሬር የሚመራው ኡማ ፓርቲ እና የሱዳን ኮንግረስ ፓርቲን ጨምሮ ዋና ዋና የሲቪል ጥምረቶች እና የፖለቲካ ፓርቲዎች የአፍሪካ ሕብረትን አቋም ያለጊዜው የተወሰደ ሲሉ ውድቅ ያደረጉት ሲሆን፣ ሂደቱ ግልጽ የመሳተፊያ መስፈርት የሌለው እና በጦር ሜዳ የተገኘን የበላይነት ወደ ፖለቲካዊ ጥቅም ለመቀየር ያለመ ነው ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

የሶሙድ ጥምረት እና የአብደል ዋሂድ አል-ኑር የሱዳን ነፃነት ንቅናቄ (SLM-AW) ስብስብ የሆነው የመርሆች ስምምነት ኃይል በበኩሉ የአፍሪካ ኅብረት በሰራዊቱ የሚመራውን ሂደት መደገፉ «ኃላፊነት የጎደለው» ተግባር ነው ሲል ከሷል።

ቡድኑ ባወጣው መግለጫ «እንቅስቃሴው በጦርነቱ ተሳታፊ በሆነው በአንዱ ወገን እና በቁጥጥሩ ስር ባሉ አካባቢዎች የሚካሄድ በመሆኑ ጦርነቱን ለማቆም ሳይሆን የጦርነቱን መቀጠል ቅቡል ለማድረግ የተደረገ ነው» ሲል ገልጾ፣ አስተማማኝ የተኩስ ማቆም ሳይደረግ በወታደራዊ ቁጥጥር ስር ውይይት ማካሄድ የሀገሪቱን ክፍፍል ያጠናክራል ሲል አስ አሳስቧል።

ዘገበው የ አዲስ ስታንዳርድ ነው
September 1, 2026 197