በሕይወት ትልቁ ቁም ነገር ትምህርት መውሰድ ነው፡፡
መቼም በስለንም አውቀንም አንጨርስም። ባወቅን ቁጥር ብዙ ቀዳሚ አላዋቂነታችን ይታወሰናል፡
ሁሌም እንማር፣
ሁሌም ለመለወጥ ዝግጁ እንሁን፣
ሁሌም ብሩሕ ተስፋ ይኑረን፡፡
ብልህ ሰው ዛሬ ላይ ፡
ዐዋቂ ነኝ፣
ትክክል ነኝ፣
እኔ ብቻ የሚል ሳይኾን ዛሬ ላይ የሕይወትን ትምህርት ከሕፃናት ሳይቀር ለመማር የተዘጋጀ ነው፡፡
ስለ ዛሬ ማንነቱ ሲያስብ ሙሉነት የሚሰማው ብቻ ሳይሆን፣ ነገ ላይ ለመሙላት የሚሰናዳ ነው፡፡
ብልህ ሰው ትናንትናንና ነገን አስታርቆ ዛሬን በእረፍት በእርጋታና በደስታ የሚኖር ሲሆን፣ በሰው ሁሉ ለመወደድ ሳይሆን መልካም ሰራ ሰርቶ በጌታው ለመውደድ የሚጥር ነው፡፡
@excellence_tutorial_tips
2November 2, 2025 603 1