ኤክሰለንስ ቤት ለቤት አስጠኚ: post #1086 — TG.ME

⭐️የ8ኛ እና 6ኛ ክፍል የመልስ መስጫ ወረቀት አጠቃቀም መመሪያ ለተማሪዎች፣ ⭐️➊ የተማሪዎች መለያ ቁጥር እና የትምህርት ዓይነት መለያ ቁጥር ለእያንዳንዳቸው በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ከላይ ወደ ታች መፃፍ አለበት፡፡ ✅❷ በተፃፈው መለያ ቁጥር ፊት ለፊት የተፃፈውን ቁጥር የያዘውን አራት ማዕዘን ቅንፍ (Square Bracket) ብቻ ማጥቆር አለበት፡፡ ⭐️➌ ተማሪዎች የመረጡትን መልስ ትይዩ በተሰጠው አራት ማዕዘን ቅንፍ (Square Bracket) ላይ በትክክል ማጥቆር አለባቸው፡፡ ✅❹ ተማሪዎች ያጠቆሩትን መልስ መቀየር ቢፈልጉ መጀመሪያ ያጠቆሩትን የአራት ማዕዘን ቅንፍ (Square Bracket) በደንብ ማጥፋት አለባቸው፡፡ ⭐️❺ በአንድ ረድፍ ከአንድ በላይ መልስ (የአራት ማዕዘን ቅንፍ/Square Bracket) ማጥቆር የተከለከለ ነው፡፡ ✅❻ ለመፃፍ እና ለማጥቆር ከተፈቀደው ቦታ ውጭ ምንም አይነት ፅሁፍም ሆነ ጭረት ማድረግ የተከለከለ ነው፡፡ ⭐️❼ ለመፃፍ ከተፈቀደው ቦታ ውጭ ተፅፎ ወይም ትንሽ ጭረት እና ነጥብ ከተገኘ የመልስ መስጫ ወረቀቱ ሙሉ  በሙሉ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ ✅❽ መልስ በሚጠቆርበት ጊዜ እርሳሱ ከተሰጠው አራት ማዕዘን ቅንፍ (Square Bracket) መውጣት የለበትም። ከወጣም በማጥፊያ ማጥፋት ይጠበቅባችኋል። ⭐️❾ መልስ መስጫ ኮርነር ላይ ያሉትን አራት ጠርዞች መንካትም ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡ ✅➓ ተፈታኞች የመልስ መስጫ ወረቀታቸውን በንፅህና መያዝ አለባቸው ማለትም እንዳይቆሽሽ፣ እርጥበት  እንዳይነካው፤ እንዳይቀደድ እና እንዳይታጠፍ መጠንቀቅና ሙሉ ኃላፊነት መውሰድ አለባቸው፡፡ ⭐️⓫ በእስክሪብቶ መፃፍ አይፈቀድም። ስለዚህ እርሳስ፣ ላጲስ እና መቅረጫ አይለያችሁ ✅⓬ ፈተና ጨረስኩ ብሎ አላስፈላጊ የሆነ ነገር፤ ስዕል ወይም ሌላ ከጀርባም ይሁን ከፊት አይፃፍበትም። ⭐️⓭ በጣም የተቀረፀ ሹል እርሳስ በምንጠቀም ወቅት ወረቀቱ እንዳይቀደድ መጠንቀቅ አለብን። ⭐️⭐️⭐️⭐️  ⭐️ ⭐️መልካም ፈተና⭐️ ⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️ @excellence_tutorial_tips

June 10, 2025 662 2