በድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ከ1 ሺህ 534 ኪሎ ሜትር በላይ የመንገድ ጥገና ሥራዎች ተከናወኑ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 01/2018 (ኢ መ አ)፦ በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የድሬዳዋ መንገድ አውታር አሥተዳደር ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት በ2018 በጀት ዓመት ከ1 ሺህ 534 ኪሎ ሜትር በላይ የሚሸፍን የመንገድ ጥገና በማከናወን ከዕቅድ በላይ አፈጻጸም አስመዝግቧል።
በበጀት ዓመቱ ከተከናወኑ ጠቅላላ ሥራዎች ውስጥ 1 ሺህ 431 ነጥብ 4 ኪሎ ሜትሩ መደበኛ የመንገድ ጥገና ሲሆን፣ ቀሪው 102 ነጥብ 9 ኪሎ ሜትር ደግሞ ወቅታዊ የመንገድ ጥገና ነው። እነዚህ ተግባራት የመንገዶቹን የጉዳት መጠንና ዓይነት መሠረት በማድረግ በወቅታዊ፣ በመደበኛ እና በከባድ የጥገና ዘርፎች የተከፋፈሉ ሲሆን፣ ሥራዎቹም በጽሕፈት ቤቱ ራስ-ኃይል፣ በመንግሥትና በግል ሥራ ተቋራጮች አማካኝነት ተከናውነዋል።
በበጀት ዓመቱ ከተከናወኑ ዋና ዋና ፕሮጀክቶች መካከል የሚከተሉት በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳሉ፦
· ደንገጎ-ሐረር (ማያ ከተማ) አስፋልት ማንጠፍ
· አዋሽ-ሚሌ መደበኛ ጥገና
· ሐረር-ቦንባስ ወቅታዊ ጥገና ፕሮጀክቶች
የእነዚህ ቁልፍ የትራንስፖርት መስመሮች በመጠገናቸው የተጠቃሚዎችን የጉዞ ጊዜና ወጪ በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ የተቻለ ሲሆን፣ አስተማማኝ የመንገድ ደኅንነትና ምቾትም ተፈጥሯል። ከዚህ በተጨማሪም የሀገሪቱ የወጪና ገቢ ንግድ እንቅስቃሴ ይበልጥ ፈጣንና ቀልጣፋ እንዲሆን የጎላ አስተዋጽዖ አድርጓል።
ጽሕፈት ቤቱ ከዋናው የጥገና ሥራ ጎን ለጎን የመሬት መንሸራተት መከላከልና የድንገተኛ አደጋ ምላሽ አሰጣጥን ጨምሮ መጠነ-ሰፊ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል። በአዲሱ የ2019 በጀት ዓመትም የማሽነሪ፣ የማቴሪያልና ሌሎች አስፈላጊ ግብዓቶችን በማሟላት የመንገድ ጥገና ሥራዎችን ይበልጥ ለማጠናከር ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ ይገኛል።
ኢትዮጵያን የማገናኘት 75 ዓመታት
መንገዳችን፤ ኃላፊነታችን!
በተጨማሪ
› አጭር መልዕክት 8561
› ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770
› ድህረገጽ www.era.gov.et
› ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et
› ቴሌግራም https://t.me/ethioroads
› ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd
› ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads
› ኢሜል [email protected]
› ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads
Telegram
ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር
Official ERA Telegram Channal
በዚህ የቴሌግራም ቻናል
የመንገድ ዜናዎችን
የስራና የመንገድ ጨረታ ማስታወቂያዎችን
የመንገድ ፎቶዎች እና አጫጭር ቪዲዮችን ያገኛሉ።

7
2August 7, 2026 4.6K 2