ጌች አዲሱን ዌብሳይታችሁን በዚህ ልክ እንዴት ልታሰራው ቻልክ?" ስራዎች ሰው ተኮር ሲሆኑ የተሻሉ ናቸው። ሰው… — Ethio Computer School — TG.ME

"ጌች አዲሱን ዌብሳይታችሁን በዚህ ልክ እንዴት ልታሰራው ቻልክ?"

ስራዎች ሰው ተኮር ሲሆኑ የተሻሉ ናቸው። ሰው የት እንደሚገናኝ አይታወቅም። ባለፉት ጊዜያት እኔ ለራሴ ብዬ የሰራኋቸውን ትምህርቶች ሰዎች "ባንተ ምክንያት እንደዚህ ሆንኩ፣ ህይወቴ ተቀየረ" ሲሉኝ ሳይ በጣም አስገረመኝ። ሌላው ደግሞ የማልገምታቸው ቦታዎች ላይ ሰዎችን አገኛለሁ ብዬ አስቤ አላውቅም። ከሃገር ውጭ፣ Plane ውስጥ፣ Embassy፣ Airport፣ የመንግስት ቢሮዎች ላይ ምን ልበላችሁ ብቻ ብዙ ቦታዎች ላይ ስሜን እንኳን አያውቁትም ግን Ethio Computer ይሉኛል። 😊

እንደ ቀልድ አንድ ቀን ለምን አልሰራም ብዬ በመጣልኝ ሃሳብ ተነሳሽነት የስልክ እና የኮምፒውተሬን Record ብቻ በማድረግ ለዚህ ሁሉ ህዝብ Useful ከሆንኩኝ አሁን ደግሞ የራሴን Kingdom መገንባት ያስፈልገኛል ብዬ ተነሳሁ።

ከዚህ በፊት በነበረን ስርአት ብዙ ተማሪዎች እኛ ጋር ተምረው ተለውጠው ወደራሳቸው መንገድ ይሄዳሉ። ነገር ግን በአጋጣሚ Live ላይ ስሆን ወይም በአካል ሲያገኙኝ ነው የሚነግሩኝ፣ እኔ ግን አላውቃቸውም።

በአዲሱ System የአንድን ተማሪ ሙሉ Data ማወቅ ስላለብን፣ Classes በምን ያህል ፍጥነት እየተከታተለ ነው የሚለውን ሙሉ መረጃ ማወቅ ያስችለናል። Live Chat ማድረግ ያስችላል፣ Note መፃፍ ያስችላል፣ ለክላሱ የሚያስፈልጉ Materials በስርአት እና በጥራት ተቀምጠዋል። ተማሪዎቻችን እንዳይሰላቹ እና አዳዲስ Updates ሲመጡ እንዲመለከቱ ከ TikTok የወሰድነውን Feature ጨምረንበታል።

Ethio Computer School Website ብቻ ሳይሆን ዲጂታል አለም ላይ ያለ አንድ ግዛት ነው።

https://www.ethiocomputer.school/
❤27❤‍🔥4🙏2🔥1
June 5, 2026 11.3K 5