📌ፍልሰታ ጾም ( ሱባኤ)
📝""አቤቱ የሆነብንን አስብ ተመልከት""
ሰቆቃ ኤር. ፭፥፩
♣ በሀገራችን ኢትዮጵያ መቼም በማይረሳ የሀዘን ሰቆቃ ፦ ካህናት ሲገደሉ፤ አብያተክርስቲያን ሲቃጠሉ ፤ ወገኔ እየተገደለ ሀብት ንብረቱ ሲዘርፍ አምላክ ሆይ የሆነብንን አስብ በማለት በዚህ ሱባኤ እንዲህ ብለን እንማፀን ኃይላችን እሱ ነውና ፦፦፦፦
♣"ልባችንን ከእጃችን ጋር በሰማይ ወዳለው ወደ እግዚአብሔር እናንሣ።"
(ሰቆቃው ኤርምያስ ፫: ፵፩) እግዚኦ ማሀረነ እንበል ፦፦
♣" እግዚአብሔር ከሰማይ እስኪጐበኝና እስኪመለከት ድረስ ዓይኔ ሳታቋርጥ ዝም ሳትል እንባ ታፈስሳለች።"
(ሰቆቃው ኤርምያስ ፫: ፵፱-፶) እንዳለ ነብዩ በእንባ እንማፀን ወደ ጌታ፦፦
♣" ስለ ምን ለዘላለም ትረሳናለህ? ስለ ምንስ ለረጅም ዘመን ትተወናለህ?"
(ሰቆቃው ኤርምያስ ፭:፳) መከራውን ከእኛ እንዲያርቅ እንለምን ፦፦
♣" አምላካችን ሆይ፥ አንተ አትፈርድባቸውምን? ይህን የመጣብንን ታላቅ ወገን እንቃወም ዘንድ አንችልም፤ የምናደርገውንም አናውቅም፤ ነገር ግን ዓይኖቻችን ወደ አንተ ናቸው።"
(መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ ፳፡ ፲፪)
በማለት ፍርዱን ለፈጣሪ እንስጥ፦፦
♣" አቤቱ፥ ማረን አንተን ተማምነናል፤ ጠዋት ጠዋት ክንድ በመከራም ጊዜ ማዳን ሁነን።"
(ትንቢተ ኢሳይያስ ፴፫: ፪) መታመኛችን እሱ ነውና ዘወትር የምህረት ክንዱን እንዲዘረጋልን ማረን እንበል ፦፦
♣" ማረን አቤቱ ማረን"
(መዝሙረ ዳዊት ፼፳፫: ፫) ዛሬ ዐይናችን ያየነውን ፣ ጃሮአችን የሰማውን የመረረ ሀዘንና መከራ ከእኛ እንዲያርቅ በሱባኤው ማረን አቤቱ ማረን እንበል ፤ የሞቱትን ነፍስ ይማር ፤ የተጎዱትን ጨርሶ ምህረቱን ይላክልን ፣ ለሕዝቡ መጽናናትን ያድልልን፤ ቤተክርስቲያችንን ከክፉ ይጠብቀልን ፤ ሀገራችንን ኢትዮጵያንን ሰላም ያድርግልን፤ ለዘመናት ተዋዶና ተከባብሮ የኖረውን ክርስቲያኑና ሙስሊሙን ለመለያየት እሳት የሚያፍሙትን ልቦና ይስጥልን!!!! ሱባኤውን በሰላም አስጀምሮ እንዲያስጨርሰን የእርሱ መልካም ፈቃድ ይሁን!!!!
👉የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በረከት እና ረድኤት በሁላችን ይደርብን ፦ መልካም ሱባዔ🙏
📍ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ

97
5
3
1August 6, 2026 6K 19 12