ለምን ይዋሻል ...? 👉ዛሬ በወጣው መረጃ ፣ የሃይማኖት ተቋማት የምሥረታ በዓሉን ሲከናውን ፣ ከፍተኛ… — ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ ( Ethio Beteseb Media) — TG.ME

📝ለምን ይዋሻል ...?

👉ዛሬ በወጣው መረጃ ፣ የሃይማኖት ተቋማት የምሥረታ በዓሉን ሲከናውን ፣ ከፍተኛ የብልጽግና ሹማምንት እና የተለያዩ ሃይማኖት አባቶች መገኘታቸውን በፎቶ መዘገቡን አይተናል ፦

👉በዚህ መርሀግብር ላይ በቀጥታ ሥርጭት ላይ ቅዱስ ፓትርያርኩ እንደተገኙ ተደርጎ ሁለት ጊዜ በEOTC TV ፎቶአቸው መለጠፉ ለምን አስፈለገ ? ምን ታስቦ ነው ? ቅዱስ ፓትርያርኩ በፍፁም አልተገኙም ።

👉ልምሾ የሆነው የሃይማኖት ተቋም በዋነኛነት የሚያስፈጽመው የብልጽግናን አጀንዳ ነው ፣ ሀገር ሰላም አጥታ ፣ በየክፍለሀገሩ የብዙዎች ደም ይፈሳል በዘራቸው እና በሃይማኖታቸው ምክንያት በየቀኑ ይገደላሉ። እንደ ሃይማኖት ተቋም በዚህ ጉዳይ መምከር ሲገባው ፣ ካድሬ ሰብስቦ ዛሬ ሰላም ሰፍኗል ይለናል ሃይማኖት ተቋም ተብዬው ።

👉ቅዱስ አባታችን ስለሳላም በእንባ ዛሬ አይደለም መናገር የጀመሩት ፣ ሰሚ ጠፍቶ ይኽው ዛሬ ድረስ ፣ የብዘዎች ደም በከንቱ ይፈሳል ። EOTC TV የሚያዘው ማን ነው ? ፣ የቤተክርስቲያኑ የመጨረሻው መሪ ፣ ባልተገኙበት እና መልእክት ባላስተላለፉበት ፎቶአቸውን ፊት ለፊት ለጥፎ ቁማር ይጫዋታል ፣ ይህ ሲሆን ለምን ብሎ የሚጠይቅ ማንም የለም ? ምንደኛው ስለበዛ !

👉ይህን ያደረገው ተቋም ለምን እንዳደረገ ምላሽ ሊሰጥ ገባል።

📍ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ
❤51👍17🔥1
September 1, 2026 2.1K 5 3