📝የመሪዎቹ ድንዛዜ እና የሚዱያው ልክ ያለፈ ውዳሴ
👉ዛሬ ቤተክርስቲያንን የሚመሩ ናቸው የተባሉ ፣ ሁለቱ ጳጳሳት በዚሁ ከቀጠሉ ፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ እና መከራ በእጥፍ ይቀጥላል ፣
👉ዛሬ እነዚህ የሃይማኖት መሪዎች ፣ ያለልክ በሀብት የደረጁ ፣ ከኢትዮጵያ አልፈው በዱባይ ቤት እንዳላቸው የሚነገርላቸው ባለጸጋ ናቸው፣ በተለይ አንደኛው ጳጳስ ለማየት እጅግ በጣም የሚዘገንን ፣ ለሰማውም ጆሮ የሚያሲዝ ረዘም እና ዘለግ ያለ የነውር ቪዲዮ ተመልክተን እጃችንን አፋችን ላይ ጭነናል ❗🎬❗።
👉ቤተክርስቲያን ይቃጠላል ፣ ካህናት በግፍ እና በስቃይ ይገደላሉ ፣ ምዕመናኑ እንደ ሽንኩርት ይቀረደዳሉ ፣ እነሱ ግን ምን ገዶአቸው፣ ምን ጎሎባቸው ፣ መግለጫ ያለ፣ ጸሎተ ፍታት መታወጅ የለ ዝም ጭጭ።
👉 በምዕመናን ገንዘብ የ24 ሠዓት ሥርጭት የሚያከናውነው ሚዲያ ዘወትር ውዳሴ እና አድንቆቱ ጀግና የሃይማኖት መሪ እያለ እነሱን ይለጥፋል ፣ በመንግስት ቃለ አቀባዮችም ምስጋና ይቸራቸዋል ፣ እነሱም እንደ አቋም ይዘውታል ፣ መንግሥት አይከፋብን እንጂ በእኛ ላይ ሚዲያ ሆነ ሕዝብ ቢንጫጫ ማንም ምንም አያመጣም ❗❗ ገራሚ እኮ ነው።
👉ዛሬ የቤተክነቱ የሚዲያ ኃላፊዎች በልዩ ጥቅም እንክብካቤ የተያዙ ናቸው ፣ ሁለት ትልልቅ መምሪያ ደርበው ፣ የግል ጥቅም የሚያካብቱ ፣ እነሱን በማወደስ ፣ ቀራቢ ነን በሚል በከፍተኛ ገንዘብ ተቀብለው ሥራ እናስመድባለን በሚል የድለላ ሥራ የሚሰሩ እንደሆነ ይነገራል ፣ ዛሬ ሚዲያው ከተቋም ባሻገር የሁለቱ የግል ንብረት የዞረ ይመስል ከሁለቱ ጴሳት ዘገባ ውጭ ማውራት በማቆሙ በርካታ ጳጳሳት የሀገረስብከታቸውም ሚዲያ ብቻ መጠቀም ጀምረዋል ፣ ብቻ ስንቱ ይነገር ፣ ሰው በበላበት ይጮሀል ፣ የሁለቱ ፎቶዎችን የያዘውን ዘገባ ለመረጃ ከስር ይመልከቱ፦
👉ቅዱስ ሲኖዶሱ የእነዚህ ሁለት ጳጳሳት አንባገነናዊ ሥርዓት ካልገታ በእርግጠኝነት ፣ ቤተክርስቲያን ላይ የሚደርሰው ግፍ እና መከራ ፣ ከፍተኛ የገንዘብ ውብድና እና ዝርፊያ ፣ እጅግ በከፋ እና አደገኛ በሆነ መንገድ ይቀጥላል ፣ ይህ ደግሞ ስብራቱ ቀላል አይደለም ። ቅዱስ ሲኖድስ አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ አለበት ።
👉 በቅዱስ ፓትርያርኩ አጠገብ የምትገኙ ፣ ቅዱስነታቸው በሁለቱ ውንብድና እና ዝርፊያ እሳቸውን ለማስገባት ፣ እንዳሉበትም አድርጎ ምንም በማያውቁት ሥራዎች እየተሰሩ እንዳለ ሰምተናል እና ፣ በዙሪያ ያላችሁ በስተመጨረሻ ታሪክ እንዳታበላሹ ቅዱስ ፓትርያርኩን በንቃተ ኅሊና ጠብቁ ፣ ይህ ምክራችን ነው ሤራው ከቤተመንግስት እስከ ቤተክህነቱ የተዘረጋ ወጥመድ ነው ። ይቀጥላል....
ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ
23
7
1August 31, 2026 1.5K 2 3









