👉የድልድዩ ዋና መደገፊያ የድንጋይ ግንብ (Masonry Abutment /Retaining Wall) በከፍተኛ የውሃ እና የጎንዮሽ አፈር ጫና ምክንያት ተደርምሷል።
🔴 ቀዩ ቀስት (Backfill / Embankment Soil Washout)፦ ከግንቡ በስተጀርባ ያለው አፈር በውሃ መሸርሸር (Scouring) እና በውሃ ሙላት (Hydrostatic Pressure) ምክንያት ድጋፉን አጥቶ መናዱን ያሳያል።
🔵ሰማያዊ ቀስት (Masonry Retaining Wall Collapse)፦ ከባድ ጭነት የመሸከም እና አፈር የመደገፍ አቅም ያለው የድንጋይ ግንብ (Stone Masonry Abutment) ሙሉ በሙሉ የመዋቅር ስብራት አጋጥሞት መደርመሱን ያሳያል።
🟡 ቢጫ ቀስት (Bridge Superstructure / Girder Bearing Zone)፦ የድልድዩ ኮንክሪት ንጣፍ (Superstructure Slab/Deck) የሚያርፍበት የቤሪንግ (Bearing Zone) ክፍል ሲሆን፣ የመደገፊያው ግንብ በመናዱ ምክንያት የድልድዩ አካል ያለ በቂ ድጋፍ በአየር ላይ ተንጠልጥሎ ይገኛል።
⚠️ ለዚህ አደገኛ መደርመስ ዋነኛ ምክንያቶች፦
1️⃣ Lack of Weep Holes / Drainage System፦ ከግንቡ በስተጀርባ የሚከማቸውን ውሃ ለማስወጣት የሚያስችሉ የውሃ መውረጃ ቀዳዳዎች (Weep Holes) አለመኖር ወይም መደፈን፣ ይህም ከፍተኛ የውሃ ጫና (Hydrostatic Pressure) ይፈጥራል።
2️⃣ Inadequate Wall Thickness & Base Depth፦ የድንጋይ ግንቡ ውፍረት እና መሰረት ከላይ ከሚመጣው የትራፊክ እና የአፈር ጫና ጋር አለመመጣጠን።
3️⃣ Scouring Effects፦ በጎርፍ ወቅት በግንቡ ስር ያለው አፈር በውሃ ተሸርሽሮ መሄዱ (Subgrade Erosion)።
@etconp

6September 6, 2026 1.1K 7