የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ለ3ኛ ጊዜ የሀገረ ስብከት አቀፍ ፈተና ለ4ኛ ፣ ለ8ኛ እና ለ10ኛ ክፍል ከ2500 በላይ የሰ/ት/ቤት ተማሪዎች ሐምሌ 26/2018 ዓ/ም መስጠቱን አስታወቀ፡፡
የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በ2018 ዓ/ም ለ3ኛ ጊዜ የሀገረ ስብከት አቀፍ ፈተና ለ4ኛ፣ ለ8ኛ እና ለ10ኛ ክፍል የሰ/ት/ቤት ተማሪዎች 6 ፈተናዎች በየትምህርት ዓይነቱ በ2ቱም ቋንቋ (በአማርኛ እና በአፋን ኦሮሞ) በትላንትናው ዕለት ጠዋትና ከሰዓት እንዲሰጥ አድርጓል፡፡
በመንበረ ጵጵስና፣ በቢሾፍቱ አካባቢውና በአድአ፣ በአዳሚ ቱሉ፣ በሉሜ፣ በዱግዳ፣ በቦሰት እና በፈንታሌ በድምሩ በ8 የወረዳ ቤተክህነት ሥር በሚገኙ ሰ/ት/ቤቶች በተመረጡ ማዕከላዊ የምዘና ጣቢያዎች ምዘናው ተሰጥቷል፡፡
መረጃው የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሰ/ት/ቤቶች አንድነት ነው።
የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!
(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)
👉 Youtube
👉 Facebook
👉 Telegram
👉 Tiktok
👉 Website
16
5August 3, 2026 3.8K 5







