ለተከታታይ 6 ቀናት ሲካሄድ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ ነሐሴ 25/2018 ዓ.ም የሰንበት ትምህርት ቤቶች… — የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU — TG.ME

ለተከታታይ 6 ቀናት ሲካሄድ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ

ነሐሴ 25/2018 ዓ.ም የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት

በደቡብ ወሎ ሃገረ ስብከት ሰ/ት/ቤቶች አንድነት አዘጋጅነት ለ 20 ወረዳዎች ከነሐሴ 18 እስከ 23  ሲሰጥ የቆየው ስልጠና በርዕሰ አድባራት ደሴ ደብረ መድኀኒት መድኀኔዓለም ቤተክርስቲያን የደቡብ ወሎ ሃገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መምህር ቆሞስ አባ ለይኩን ወንድይፍራው ፣ የሃገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ ሊቀ ኅሩያን ፍቅረ ኢየሱስ ተሰማ ፣ መልአከ ብርሃን ኪሮስ ፋሲል የደሴ ከተማ አስተዳደር ቤተ ክህነት ዋና ስራአስኪያጅ ፣መምህር ተስፋማርያም ቢሰጠኝ የደቡብ ወሎ ሃ/ስብከት የስብከተ ወንጌል እና የሰንበት ትምህርት ቤት ክፍል ሐላፊ የአድባራት አስተዳዳሪዎች ፣የሰበካ ጉባኤ አባላት የሰ/ት/ቤት አመራሮች እንዲሁም ስልጠናውን በደሴ ደብረ ቤቴል ቅድስት ሥላሴ እና ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል በሚገባ ሲከታተሉ የቆዩ ሰልጠኞች በተገኙበት እጅግ በደማቅ መርሃግብር ስልጠናው የተጠናቀቀ ተጠናቀቀ።

በመርሃግብሩ ላይ ትምህርት፣የደቡብ ወሎ ዘሃገረ ስብከት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት አጠቃላይ ሪፖርት ፣ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ በመጡት በ መምህር ያሬድ ስልጠና ፣ ቅኔ እንዲሁም በስልጠናው ላይ ለተሳተፉ እና ስልጠናው እንዲከናወን ድጋፍ ላዳረጉ አካላት የምስጋና የምስክር ወረቀት በመስጠት በመጨረሻም የደቡብ ወሎ ሃገረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ በመምህር ቆሞስ አባ ለይኩን ቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች እና መልእክቶች ተላልፈው መርሃግብሩ ተጠናቋል።

በተያያዘም የደቡብ ወሎ ሃገረ ስብከት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤውን አካሂዷል።

መረጃው የደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ነው።

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok

👉  Website
❤13👍2👏1
August 31, 2026 1.9K 6