በኬንያ የተመዘገቡ የሳይበር ስጋት ክስተቶች ቁጥር 11 ቢሊዮን ማለፉ ተገለጸ
የኬንያ የኮሙዩኒኬሽን ባለሥልጣን በ2025/26 በጀት ዓመት በሀገሪቱ የዲጂታል መሠረተ ልማት እና የመረጃ ሥርዓቶች ላይ የተቃጡ 11.12 ቢሊዮን የሚጠጉ የሳይበር ስጋት ክስተቶች መመዝገባቸውን አስታወቀ። ይህም ባለፈው የበጀት ዓመት ከተመዘገበው 8.62 ቢሊዮን የሳይበር ስጋቶች ጋር ሲነጻጸር የ29 በመቶ ገደማ ዕድገት ያሳየ መሆኑን የሀገሪቱ የሳይበር ደህንነት ማዕከል (KE-CIRT/CC) ይፋ ያደረገው መረጃ ያመለክታል። በተለይም ከሚያዝያ እስከ ሰኔ ባለው የሩብ ዓመት ወቅት ብቻ ከ4.5 ቢሊዮን በላይ የሳይበር ስጋት ክስተቶች በቁጥጥር ሥርዓቱ አማካኝነት ተለይተዋል።
ይህ የተመዘገበው ከፍተኛ ቁጥር በሀገሪቱ የኦንላይን የፋይናንስ እንቅስቃሴዎችና የዲጂታል አገልግሎቶች መስፋፋታቸውን የሚያሳይ ቢሆንም፤ ሁሉም የተመዘገቡ ስጋቶች ስኬታማ የሳይበር ጥቃቶች ወይም የውሂብ መንተፍ ክስተቶች አለመሆናቸውን ባለሥልጣኑ አብራርቷል። ይልቁንም ቁጥሩ አብዛኞቹ ጥቃቶች በደህንነት ሥርዓቶች አማካኝነት አስቀድመው መታገዳቸውንና መክሸፋቸውን ያመላክታል። በመሆኑም የንግድ ተቋማትና ኩባንያዎች የሀገሪቱን አጠቃላይ የሳይበር ስጋት መረጃዎች መነሻ በማድረግ የራሳቸውን የመከላከል አቅም፣ የሶፍትዌር ማዘመኛዎችን እና የሠራተኞች ግንዛቤ እንዲያጠናክሩ ተመክሯል።
🔗 TechTrends KE
#Cybersecurity #Kenya #TechNews

TechTrendsKE
Turning Kenya’s national cyber threat statistics into actionable business security priorities
Kenya recorded more than 11.12 billion cyber threat events in FY2025/26. The number matters, but detected events, attempted attacks and confirmed breaches are different measures.
October 24, 2026 12