የኢትዮጵያ ካፒታል ማርኬት ባለስልጣን የህብረት ኢንቨስትመንት አሰራር መመሪያ ይፋ አደረገ የኢትዮጵያ ካፒታል…

የኢትዮጵያ ካፒታል ማርኬት ባለስልጣን የህብረት ኢንቨስትመንት አሰራር መመሪያ ይፋ አደረገ

የኢትዮጵያ ካፒታል ማርኬት ባለስልጣን (ECMA) በሀገሪቱ የመጀመሪያ የሆነውን የህብረት ኢንቨስትመንት መርሃ ግብሮች (Collective Investment Schemes) አሰራር መመሪያ ይፋ አደረገ። መመሪያ ቁጥር 1150/2026 ተራ ዜጎች፣ ኩባንያዎች እና ተቋማት ገንዘባቸውን በማሰባሰብ በሙቹዋል ፈንዶች፣ በገንዘብ ገበያ ፈንዶች፣ በሪል እስቴት እና በ ETFs ላይ ፈቃድ ባላቸው የኢንቨስትመንት አስተዳዳሪዎች አማካኝነት በጋራ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ህጋዊ ማዕቀፍ ይፈጥራል። መመሪያው ስድስት የተለያዩ የኢንቨስትመንት አይነቶችን የፈቀደ ሲሆን፣ የኢንቨስተሮች ንብረት እና ገንዘብ ደህንነት በገለልተኛ የባንክ Custodian እንዲጠበቅ እና ግልጽ አሰራር እንዲኖር ግዴታ ይጥላል።

ይህ አዲስ መመሪያ ከዚህ ቀደም በባንክ ቁጠባ እና በቤት ወይም መሬት ላይ ብቻ ተወሰኖ የነበረውን የሀገር ውስጥ የኢንቨስትመንት ባህል በመቀየር ለብዙሃኑ ዜጎች የካፒታል ገበያ ተሳትፎ መንገድ ይከፍታል ተብሏል። እንደ ኬንያ እና ኡጋንዳ ያሉ የጎረቤት ሀገራት ልምድ እንደሚያሳየው፣ መሰል የህብረት ኢንቨስትመንት ምርቶችን ከዲጂታል ክፍያዎች እና የሞባይል ፕላትፎርሞች ጋር በማቀናጀት የኢንቨስተሮችን ቁጥር እና የፈንድ መጠን በአጭር ጊዜ ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ ተችሏል።

🔗 Capital Ethiopia
#Ethiopia #CapitalMarket #Fintech
October 25, 2026 18