የደቡብ አፍሪካው ISPA ለዝቅተኛ ገቢ ያላቸው አባወራዎች ነፃ የዳታ አቅርቦት እንዲመቻች ጠየቀ
በደቡብ አፍሪካ የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢዎች ማህበር (ISPA) አነስተኛ ገቢ ላላቸው አባወራዎች ነፃ የመሰረታዊ ዳታ አቅርቦት እንዲመቻች እና የኢንተርኔት መጠቀሚያ መሳሪያዎች ዋጋ እንዲቀነስ ጥሪ አቀረበ። ማህበሩ የመንግስት የኮሙዩኒኬሽን እና የዲጂታል ፖሊሲዎች ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚው ለማስገባት የታለሙ ቢሆኑም፣ አፈጻጸማቸው ግን አሁንም ወደኋላ የቀረ መሆኑን ገልጻል። በተለይም በሀገሪቱ የስማርትፎን መሳሪያዎች እንደ ቅንጡ ዕቃ ተቆጥረው ከፍተኛ ታክስ የሚጣልባቸው መሆኑ ለአነስተኛ ገቢ ተጠቃሚዎች ትልቅ ፈተና ሆኗል።
የደቡብ አፍሪካ ኮሙዩኒኬሽን እና ዲጂታል ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከሞባይል ኦፕሬተሮች እና ከፋይናንስ ሚኒስቴር ጋር በመነጋገር የታክስ እና የዳታ ዋጋ ማሻሻያ ለማድረግ ቢያቅድም፣ እስካሁን ግልጽ እርምጃ አልተወሰደም። በተጨማሪም የሀገሪቱ የቴሌኮም ተቆጣጣሪ አካል ICASA ያወጣቸው አዳዲስ የደንበኞች መብት መመሪያዎች በ Vodacom እና MTN በኩል የህግ ክስ ገጥሟቸዋል። ISPA እውነተኛ የዲጂታል ተዳራሽነትን ለማረጋገጥ የዳታ ዋጋን በመቀነስ ላይ ብቻ ሳይሆን፣ አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች በቀጥታ በሚደግፉ አሰራሮች ላይ መስራት እንደሚገባ አሳስቧል።
🔗 ITWeb Africa
#InternetAccess #SouthAfrica #Telecom
ITWeb
ISPA urges free data for poor households
High costs continue to exclude low-income South Africans from the digital economy, says the Internet Service Providers’ Association.

October 20, 2026 20