የ Dangote ሪፋይነሪ አክሲዮን በኢትዮጵያ መግዛት የሚችሉት 100 ብቁ ባለሃብቶች ብቻ እንደሆኑ ተገለጸ
Aliko Dangote በናይጄሪያ የሚገኘውን የአፍሪካ ግዙፍ የነዳጅ ማጣሪያ Dangote Refinery አክሲዮኖችን በኢትዮጵያ ለመሸጥ በአዲስ አበባ የኢንቨስተሮች ማስተዋወቂያ መድረክ አካሂደዋል። ሆኖም በ Ethiopian Capital Market Authority (ECMA) መመሪያ መሠረት፣ ሽያጩ የተፈቀደው ለ 100 ብቁ ኢንቨስተሮች (Qualified Investors) ብቻ ነው። እነዚህም ባንኮችን፣ የኢንሹራንስ ኩባንያዎችን እና ከመኖሪያ ቤትና መኪና ውጪ ቢያንስ 10 ሚሊዮን ብር የተጣራ ሀብት ያላቸውን ግለሰቦች የሚያጠቃልል ሲሆን፣ መደበኛ አነስተኛ ኢንቨስተሮች (Retail Investors) በሂደቱ መሳተፍ አይችሉም።
አንድ አክሲዮን በ 74.90 ብር የተመደበ ሲሆን፣ አነስተኛው የግዢ መጠን 10 አክሲዮን ወይም 749 ብር ነው። Dangote Industries በድምሩ 4.1 ቢሊዮን አክሲዮኖችን በመሸጥ 1.56 ቢሊዮን USD ለመሰብሰብ አቅዷል። የ ECMA ዋና ዳይሬክተር Dagmawit Sheferaw ከናይጄሪያ ጋር ያለው የሕግ ማዕቀፍ ማጣጣም ባለመጠናቀቁ መደበኛ ኢንቨስተሮች እንዳልተካተቱ ገልጸው፣ በቀጣይ ፍላጎት ካለ መመሪያው ሊሻሻል እንደሚችል ጠቁመዋል። አቅርቦቱ እስከ October 27 ክፍት ሆኖ ይቆያል።
🔗 Shega
#Investment #Ethiopia #ECMA

Shega
Dangote’s Ethiopian Share Sale Runs Ahead of the Rulebook
Dangote’s refinery reported $1.82 billion in profit after tax in the first half of 2026, following losses in 2024 and 2025. The company is now seeking capital to help fund a $14.3 billion expansion that would lift refining capacity to 1.4 million barrels…
1October 17, 2026 174