Airtel Money በለንደን የአክሲዮን ገበያ በ7 ቢሊዮን USD ግምት መመዝገቡን ይፋ አደረገ
የ Airtel Africa የሞባይል ገንዘብ ክፍያ ድርጅት የሆነው Airtel Money በለንደን የአክሲዮን ገበያ (London Stock Exchange) አክሲዮኖቹን ይፋዊ ሽያጭ ማካሄድ ጀምሯል። በዝርዝሩ መሠረት የአንዱ አክሲዮን ዋጋ 1.96 ፓውንድ (2.60 USD) የተመነዘረ ሲሆን ይህም የኩባንያውን አጠቃላይ ዋጋ 7 ቢሊዮን USD አድርሶታል። በዚህ የመጀመሪያ ደረጃ የአክሲዮን ሽያጭ እንደ Mastercard፣ Qatar Holding እና TPG ያሉ ነባር ባለሃብቶች የ529 ሚሊዮን ፓውንድ (700 ሚሊዮን USD) አክሲዮኖችን የሸጡ ሲሆን፣ International Finance Corporation (IFC) ደግሞ የ90 ሚሊዮን USD አክሲዮኖችን በመግዛት ተሳትፏል። ይህ ክስተት በለንደን የአክሲዮን ገበያ ባለፉት አምስት ዓመታት ከተካሄዱት ትልልቅ የአክሲዮን ሽያጮች አንዱ ሲሆን፣ በዓለም አቀፍ ገበያ የተመዘገበ የመጀመሪያው ግዙፍ የአፍሪካ ፊንቴክ አድርጎታል። በ13 የአፍሪካ አገራት 53 ሚሊዮን ንቁ ተጠቃሚዎች ያሉት Airtel Money፣ ባለፈው የሂሳብ ዓመት 1.35 ቢሊዮን USD ገቢ ማግኘቱን እና የ373 ሚሊዮን USD ትርፍ ማስመዝገቡን ገልጿል። ይህም የአፍሪካ የፊንቴክ ዘርፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ እያደገ የመጣውን ተፅዕኖ የሚያሳይ እንደሆነ ተገልጿል።
🔗 Benjamindada
#Fintech #AirtelMoney #Africa

Condia
Investors sell down Airtel Money stakes as London listing
Airtel Money began trading on the London Stock Exchange on Wednesday under the ticker AMC, after an IPO priced at £1.96 ($2.60) a share.
October 15, 2026 32