ምስጋና ለሁሉም! የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለ46 ቀናት ሲያከናውነው የቆየው የምክክር መድረክ በሰላም… — የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC — TG.ME

🇪🇹 ምስጋና ለሁሉም!
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለ46 ቀናት ሲያከናውነው የቆየው የምክክር መድረክ በሰላም በመጠናቀቁ ደስታችንንና ምስጋናችንን እንገልጻለን።
በዚህ ረጅምና አስፈላጊ የምክክር ሂደት በኃላፊነት፣ በትዕግሥትና በመከባበር ለተሳተፉ ተሳታፊዎች፣ ለኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች፣ ውይይቱን በትጋት ሲያስተባብሩ ለነበሩ ባለሙያዎችና ሠራተኞች ከልብ የመነጨ ምስጋናችንን እናቀርባለን።
በተጨማሪም ተሳታፊዎች በሰላም ወጥተው እንዲገቡና መድረኩ በሰላም እንዲካሄድ፣ ከፈጣሪ ጥበቃ በታች ቀንና ሌሊት የደኅንነትና የሰላም ጥበቃ ሲያደርጉ ለነበሩ ሁሉ ልዩ ምስጋናችን ይድረስ።
ለመላው ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ይህንን የምክክርና የሰላም ጉዞ በጋራ እንድንደግፍ ጥሪያችንን እናቀርባለን። ልዩነቶቻችንን በውይይት እያቀራረብን፣ የሚያግባቡንን የጋራ እሴቶች እያጠናከርን፣ ለትውልድ ሰላማዊ፣ የተረጋጋችና የበለጸገች ኢትዮጵያን በጋራ እንገንባ።
ሰላም የሁላችንም ነው፤ ለሰላም መሥራትም የሁላችንም ኃላፊነት ነው! 🇪🇹

የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል
የወንጌል አማኞች ድምፅ

የ Evangelical Media/Council የዩቲዩብ ቻናልን
ሰብስክራይብ ለማድረግ ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ
• YouTube: https://youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
• TikTok: https://www.tiktok.com/@evangelical.media
• Telegram: https://t.me/EGBCC
• Website: ecgbc.org
የቤተሰባችን አባል ለመሆን Follow, Subscribe, Like እና Share በማድረግ አብረውን ይሁኑ!
ለዜና ሽፋን መልአክት ለመላክ
t.me/evangelicalmedia
📞251 991827226 ላይ ያገኙናል
👎10❤6👍1
August 22, 2026 3K 2 2