ኦርቶቶሜኦ የእውነትን ቃል በትክክል መክፈል የተሰኘውና በመጋቢ ቤዛዓለም በላይ የተዘጋጀው አዲስ መጽሐፍ ተመረቀ።
በመጽሐፍ ምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የክብር እንግዳ ሆነው የተገኙት የኢትዮጵያ ምስጋና ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ፕሬዚዳንት ፓስተር ጌታሁን ነሲቡ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን መጽሐፉ ለምእመናንና ለቤተክርስቲያን ያለውን ጠቀሜታ በመግለጽ የተሰማቸውን ታላቅ ደስታ አጋርተዋል።
በምረቃው ላይ የመጽሐፉን ይዘት አስመልክቶ አስተያየታቸውን የሰጡት የቋንቋ ጥናት ባለሙያው አቶ አሺኔ አስቴን በበኩላቸው መጽሐፉ የወቅቱን ፍላጎት ያገናዘበና እጅግ ጠቃሚ የሆነ ሥራ መሆኑን መስክረዋል።
በማቀጠልም ወንጌላው ዙርያ ሱማ የመጽሐፉን ዳሰሳ አቅርበዋል።
የመጽሐፍ ጸሐፊ መጋቢ ቤዛ ዓለም እንደተናገሩት ኦርቶቶሜኦ" የግሪክ ቃል ሲሆን "ኦርቶ" ማለት "በትክክል" ማለት ሲሆን"ቶሚሆ" ማለት ደግሞ "መቁረጥ" ከሚለው የግሪክ ቃል የተወሰደ መሆኑ ገልጿል።በዚህ ዘመን ያሉ አገልጋዮች መጽሐፍ ቅዱስን በራሳችን አውድና ለእኛ እንደሚመቸን እያፈታን ስለሆነ ለዚያ መፍትሔ ታስቦ የተጻፈ መሆኑን አክለው ተናግራዋል።
ለኢቫንጄሊካል ዜና ቤተልሔም ደረጀ
የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል
የወንጌል አማኞች ድምፅ
የ Evangelical Media/Council የዩቲዩብ ቻናልን
ሰብስክራይብ ለማድረግ ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ
የቤተሰባችን አባል ለመሆን Follow, Subscribe, Like እና Share በማድረግ አብረውን ይሁኑ!
ለሀሳብ አስተያየት ጥቆማ በቴሌግራም
t.me/evangelicalmedia
📞251 991827226 ላይ ያገኙናል
Telegram | Facebook | Youtube | Tiktok | Website
3
2
1August 8, 2026 1.9K 4









