ሰዎችን በተጽእኖ መምራት
“ሌሎችን በተጽእኖ ለመምራት ዋነኛውና ብቸኛው ነገር ምሳሌ መሆን ነው” - Albert Schweitzer
አንድ ሰው ራሱን በትክክለኛው መልኩ መምራት እና የራስ-በራስ ተጽእኖ ማሳደር ከቻለ፣ ሌሎችን ሰዎች የመምራት አቋም እና ብርታት ላይ ራሱን ያገኘዋል፡፡ ይህ የሚሆንበት ዋነኛ ምክንያት ራሱን በመምራት ሂደት እያደገ ሲሄድ በመደበኛም ሆነ መደበኛ ባልሆነ መልኩ በአካባቢው በሚገኙ ሰዎች ላይ መልካም ተጽእኖ ማምጣት ስለሚችል ነው፡፡ ይህ አውነታ፣ “አመራር ማለት ተጽእኖ ማምጣት ማለት ነው” ከሚለው ብዙዎች ከሚስማሙበት የአመራር ትርጉም ጋር ይስማማል፡፡
ባለፈው ኃሙስ ምሽት የተጀመረውና ለሁለት ተጨማሪ ኃሙስ ምሽቶች የሚቀጥለው ስልጠና ከሚያብራራቸው እውነታዎች አንዱ ይህ ራስን የመምራት ዘርፍ ነው፡፡
ስልጠናውን ለመቀላቀል ከፈለጋችሁ ያመለጣችሁን ክፍል በድምጽ እና በጽሑፍ ግሩፑ ውስጥ ታገኛላችሁ፡፡
የስልጠናው ርእስ፡- “የአመራር እውነታዎች እና ልምምዶች” (Leadership Facts and Practices)
ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ
ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ online (telegram live)
የስልጠናው ቀናት፡- ነሃሴ 14፣ ነሃሴ 21 እና ነሃሴ 28 (ሶስት የነሃሴ ወር ኃሙሶች)
የስልጠናው ሰዓት፡- ለአራቱም ኃሙስ ምሽቶች ከ3፡00 እስከ 4፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)
በዚህ ስልጠና ለመሳተፍ፡- በዚህ 👉 @DrEyobmamo የቴሌግራም አድራሻ (user name) inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክላችኋል፡፡
Join now!!!

35
16August 22, 2026 8.9K 2 12