የትኩረት ጥቅሞች! በዚህ እጅጉን በሚያዘናጋ ዘመን፣ ትኩረትን መጠበቅ ከሁሉም የበለጠ ዋጋ ያላቸው ክህሎቶች… — Dr. Eyob Mamo — TG.ME

የትኩረት ጥቅሞች!

በዚህ እጅጉን በሚያዘናጋ ዘመን፣ ትኩረትን መጠበቅ ከሁሉም የበለጠ ዋጋ ያላቸው ክህሎቶች አንዱ እየሆነ ነው።

1. ትኩረት ዓላማችንን እንድናሳካ ይረዳናል

ትኩረታችን ካልተሰበሰበ ጊዜያችንን፣ ኃይላችንንና ጉልበታችንን በብዙ አቅጣጫ እንበትነዋለን። ትኩረት ግን በእውነት አስፈላጊ በሆነው ነገር ላይ ጊዜያችንንና ኃይላችንን እንድናውል ያደርገናል።

2. ትኩረት የአስተሳሰብ ጥራታችንን ያሻሽላል

የማያቋርጡ ማስታወቂያዎች፣ ማህበራዊ ሚዲያ፣ ብዙ መረጃና መዝናኛዎች በጥልቀት የማሰብ አቅምን ይበታትናሉ። ትኩረት ግን በጥልቀት እንድናስብ፣ እንድንረዳ፣ እንድንፈጥርና በጥበብ ውሳኔ እንድንሰጥ ያስችለናል።

3. ትኩረት ጊዜያችንን በጥበብ እንድንጠቀም ያደርጋል

ጊዜ ውስን ነው፤ ትኩረት የሚሰርቁ ነገሮች ግን ብዙ ናቸው። ትኩረት ማድረግ አስፈላጊ ባልሆኑ ነገሮች ጊዜን ከማባከን ይልቅ ውጤትና ትርጉም ባላቸው ነገሮች ላይ እንድናውለው ያስችለናል።

ይህንን አስገራሚ ክህሎት ለማዳበር የሚያግዛችሁ ንባብ ለመስከረም ወር ተዘጋጅቶላችኋል፡፡

መጽሐፉን ለማንበብ ከአሁኑ በመመዝገብ ራሳችሁን አዘጋጁ፡፡

የንባብ ወር - መስከረም / 2019

ለንባብ የተመረጠው መጽሐፍ - “ትኩረት”

ንባቡ የሚጀመርበት ቀን - መስከረም 1 / 2019

ንባቡ የሚጠናቀቅበት ቀን - መስከረም 30 / 2019

ይህንን Book Club ለመቀላቀል፡- በዚህ 👉 @DrEyobmamo የቴሌግራም አድራሻ (user name) inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክላችኋል፡፡

Join now!!!
👍12❤8
August 31, 2026 2.3K 2 5