የNarcissist ባህሪያ ያላቸው ሰዎች!
የNarcissist ባህሪያ ያላቸው ሰዎች እራሳችንን እንድንጠራጠር እንዴት ያደርጉናል?
Narcissist ባህሪ ያለው ሰው በስሜታዊ ቁጥጥር እኛ ራሳችንን፣ አስተሳሰባችንንና የምናስታውሰውን እንድንጠራጠር ሊያደርገን ይችላል።
👉 ጋስላይቲንግ (Gaslighting) – የተናገሩትን ወይም ያደረጉትን ክደው፣ “ይህ ፈጽሞ አልሆነም” በማለት የራሳችንን ትውስታና ግንዛቤ እንድንጠራጠር ያደርጋሉ።
👉 በተደጋጋሚ መተቸት – ያለማቋረጥ ድክመታችንን በመጥቀስ “እኔ በቂ አይደለሁም” ብለን እንድናስብ ያደርጉናል።
👉 ጥፋትን በእኛ ላይ መጣል – በችግሮች ውስጥ ራሳቸው ያላቸውን ሚና በመካድ፣ ለችግሩ ሁሉ እኛን ተጠያቂ ያደርጋሉ።
👉 ራሳቸውን በእኛ ላይ መንጸባረቅ (Projection) – በራሳቸው ያለውን ባህሪ ወይም አመለካከት እኛ ላይ ሊወነጅሉ ይችላሉ።
👉 የክስተቱን ታሪክ መቀየር – ነገሮችን በተለየ መልኩ በመተረክ “ምናልባት እኔ ነኝ የተሳሳትኩት” እንድንል ያደርጋሉ።
👉 ፍቅርንና ተቀባይነትን መከልከል – ፍቅራቸውን፣ ምስጋናቸውን ወይም ተቀባይነታቸውን ለማግኘት ሁልጊዜ ራሳችንን ማስተካከል እንዳለብን እንድናስብ ያደርጋሉ።
እነዚህን ሁኔታዎች አልፎ የመሄድ ጥንካሬ
· የተናገሩትንና ያደረጉትን አመኑም አላመኑም ራሳችሁን ለመጠበቅ ትክክለኛው ውሳኔ ወስኑ፡፡
· በራሳችሁ ላይ ያላችሁን አመለካከት እነሱ በሚነግሯችሁ ሃሳብ ላይ አትመስርቱ፤ እነሱን ለማሳመንም አትሞክሩ፡፡
· ሃላፊነታቸውን የመካዳቸውን ሁኔታ ለማሳየት ከመከራከር ራሳችሁን ጠብቁ፡፡
· እነሱ ያሰቡትን ያስቡ፣ የሚያወሩትን ያወሩ፤ እናንተም የራሳችሁን ኑሮ ኑሩ፡፡
· ትኩረት አትስጧቸው፣ አስፈላጊ ከሆነም ከእነሱ የመለየትን መንገድ ምረጡ (የትዳር አጋር ከሆነ ሳትቸኩሉ)፡፡
· በፍጹም ከአሁን ከአሁን ይለወጣሉ በማለት ጉዳታችሁ እስኪበረታ አትጠብቁ፡፡
መልካም ምሸት!
https://t.me/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
Telegram
Dr. Eyob Mamo
Life skill development!
You can contact me
@DrEyobmamo

39
8
5
3August 31, 2026 3.1K 7 28