ከጥሩው ወደ ምርጡ
1. ጥሩ — የመጀመር ደረጃ!
የግል ሕይወታችንን እድገትም ሆነ የምንተገብራቸውን ተግባሮች ስንጀምር በተቻለን መጠን በጥሩ ሁኔታ መጀመር አስፈላጊ ነው፡፡ አንድን ነገር ለመጀመር ፍጹም የሆንን ሰዎች መሆን የለብንም፣ ስራውንም ፍጹም በሆነ ጥራት ለመጀመር መጠበቅ የለብንም፡፡ ያለንን እውቀት፣ ክህሎትና አቅም ተጠቅመን ጥሩ የሆነ ነገር እንጀምር፡፡ መጀመር የእድገት የመጀመሪያ ደረጃ ነው።
2. የተሻለ — የመደጋገም ደረጃ!
በተቻለን መጠን በጥሩ ሁኔታ የጀመርነውን ነገር እንደገና በመመልከት እና በመገምገም የተሻለ የሚሆንበትን መንገድ መፈለግ አስፈላጊ ነው፡፡ “ምን ጥሩ ሆነ? ምን መሻሻል አለበት? ምን ማስወገድ አለብኝ? ምን መጨመር አለብኝ?” ብለን ራሳችንን እንጠይቅ። አንድ ነገር ከስህተታችን እንማር፣ ከጠንካራ ሰዎች ምሳሌ እንውሰድ፣ አዲስ እውቀት እንጨምር፣ ክህሎታችንን እናሳድግ፡፡
3. ምርጥ — ደጋግሞ የማሻሻል ደረጃ!
የግል ሕይወታችን እድገትም ሆነ የምናደርገው ነገር የተሻለ ደረጃ ደርሷል ብለን አናቁም። ካለማቋረጥ ከፍተኛ ደረጃን እንፈልግ። ጥራትን፣ ወጥነትን፣ ትክክለኛነትንና የልህቀት ደረጃን ከማሳደግ አናቁም፡፡ ምርጥ መሆን አንድ ጊዜ የሚገኝ ደረጃ ሳይሆን፣ የማያቋርጥ የማሻሻል አመለካከት ነው።
ዛሬ ጥሩ ከሆነ፣ ነገ የተሻለ እንድርገው፤ የተሻለውን ደግሞ ከዚያ የበለጠ እንድርገው።
አሁን ባለንበት ተወዳዳሪ ዓለም ውስጥ ቀድሞ የመገኛው መንገድ ይህ ነው!
https://t.me/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

3September 1, 2026 180