የሳጥናኤል ጎል በኢትዮጵያ: post #4514 — TG.ME

ከሆነ በሁዋላ የሆነውን ነገር መንገር ዜና ሲሆን;ከመሆኑ በፊት ቀድሞ መንገር ደግሞ ህዝብን እንደ ህዝብ ማስጠንቀቅና ማዘጋጀት ይባላል::
ቀደም ብለን እነዚህ ነገሮች ከመሆናቸው በፊት "...ይሆናሉና ተጠንቀቁ!አሰላለፋችሁን አጢኑ! ይህ ከባድ ቁማር ነውና በከንቱ አታጫፍሩ! ቆም ብላችሁ አስቡ! ወዘተ... " እያልን ለዓመታት ተናግረናል! ያተረፍነው የስድብ ኮመንት ብቻ ነው!
እነዚያን የመሰሉ ነጫጭ እውነቶችን ብቻ በዚህ ገጽ ስንለጥፍ በመክረማችን ምክንያትም ይህን ቻናል እና የፌስ ቡክ ገጽ ከዚህ ቁጥር በላይ ማደግ ሳይችል ቀርቶዋል!እንደ አማራ ህዝብ ባለበት የሚረግጥ ገጽ የሆነውም እውነት ብቻ የሚለጠፍበት ገጽ ስለሆነ ነው!
እውነት ደግሞ ብዙ ተከታይ የላትም!እውነትን ብቻ በመናገር ብዙ ተከታይ ማፍራት ጨርሶ አይቻልም! ያም ሆኖ ከእውነት ጋር ብቻ ብቻችንንም ቢሆን እያወራን አለን!ብዙ አድማጭና ተከታይ ቢኖረን ደግሞ ብዙ እውነቶችን ይፋ ለማድረግ ሞራል ይኖረን ነበር! አሁን አሁን ግን ብቻችንን ማውራት እየሰለቸን ሄደ መሰለኝ እንደመዛል እያልን እንገኛለን::
ለማንኛውም ነገረናል! "ነግረናል ቤት ይቃጠላል ብለናል.....!" እያልን እንደ እብድ ብቻችንን ጮኸናል ለፍልፈናል! ኅላፊነታችንንም ተወጥተናል!
በተለይ በአማራ ህዝብ ላይ እየመጣ ያለውን ከአእምሮ በላይ የሆነ ሰቅጣጭ ድርጊትን በዝርዝር ቀድመን ነግረናል!
ዛሬ ላይ ጅምር እንቅስቃሴው ወደ ተግባር እየተለወጠ ስናይ ደግሞ እንደገና ያመናል!
ጃፓናዊው ገጣሚ ዢያን ፎወን እንዲህ የሚል ግጥም አለው:
"ነጻነት በደም ይገዛል::ደም ለአገር ይለገሳል:: ደም ያላቸው ልጆች ያሉዋት በርግጥም ብሩክ አገር ናት::" ይላል:: እውነት ነው! ደም ያላቸው ልጆች ያሉዋት በርግጥም ብሩክ አገር ናት!
በዚህ በኩል ትግራዮች ዕድለኞች ናቸው! ታግለው የሚያታግሉ ለሆዳቸው ሳይሆን ለህዝባቸው ጥቅም የቆሙ ወኪሎች አሉዋቸው! የጦር ጄኔራልም ቃል አቀባይም አመራርም ሁሉም አላቸው! ይህም መታደል ነው! መጥፎነት ጥሩነት ሌላ ጉዳይ ነው:: ነገር ግን የህዝብ ወኪል የሆነ የፖለቲካ ፓርቲ ለህዝብ ጥቅም ሲል ማፈንገጥ መቻል አፈንግጦም ወደ ህዝቡ መሄድ መቻልና ከህዝቡ ጋር በጋራ ቆሞ መገኘት ዕድለኝነት ነው!
ብዓዴን አዴፓ በተባለ ቆሻሻ ድርጅት የተወከለው የአማራ ህዝብ ግን በዚህ ዘርፍ ዕድለቢስ ሆኖ እናገኘዋለን!
ብዓዴን አዴፓ የተባለው ፓርቲ የአማራ ህዝብ ወኪል ሆኖ እስከቀጠለ ድረስ የአማራ ህዝብ መቸም ቢሆን በኢትዮጵያ ምድር እንደ ዜጋ ሊቆጠር የሚችል ህዝብ አይሆንም!
የአማራ ህዝብ እነዚህን ከርሳም ባለስልጣናት በህዝብ አብዮት አስወግዶ ሌላ ወኪል ፓርቲ ካላደራጀ ከብዓዴን አዴፓ ቀንበር መላቀቅ ካልቻለ የኢትዮጵያ ዕለታዊ ዜና በሙሉ የአማራ ጭፍጨፋ ብቻ ሆኖ እንደሚቀር ዛሬም ደግመን ደጋግመን እንነግራችሁዋለን!
የዛሬ 2 ዓመትም በዚሁ ገጽ ይህንኑ እውነት ነግረናችሁ ነበር! እንዲህ በማለት::
"ዛሬ በትግራይ ክልል እየሆነ ያለው ነገር ከ 2 ዓመት በሁዋላ በአማራ ክልል በእጥፍ ይደረጋል! ብዓዴን እዴፓን ሳታስወግዱ ከሌላ ወገን ጋር መዋጋት ውሃ ቢወቅጡት እንቦጭ ነው! ስለዚህ ነገሩ እስኪጠራ ተው! ከህወሃት ጋር የማይነጻጸር ጠላት ጋር አትወግኑ! ለማይሻሻል ህገመንግስትና ለማይመለስ መሬት በከንቱ አትልፉ!ትዝብት ነው ትርፉ! ጥላቻም ቂምም ካላችሁ ለነገ አሳድሩት! ጦርነትም ከሆነ ብቻ ለብቻ የራሳችሁን ጦርነት ነገ ታደርጋላችሁ! አሁን ግን ቁማር ነውና እባካችሁ! ሃይላችሁን አታባክኑ! ታገሱ ፌደራል መንግስቱና ህወሃት ይለይላቸው! አታጫፍሩ! አማራ ማጆሪቲ ህዝብ ነውና ማጫፈር አያምርበትም! ማጫፈር ብቻ አይደለም:: ከህወሃት የበለጠ ጠላት ከሆነው ከኦነግ መንግስት ጋር ተጣምራችሁ አጉል ነገር ውስጥ አትግቡ! ቁማር ነው! ይህ ህግ ማስከበር የሚል ዘመቻ ህወሃትን ለማጥፋት የሚደረግ ጦርነት አይደለም! ይልቁንም አማራን የመጨፍጨፍ ቅድመ ስራ ነው!ቅድመ ጫካ ምንጠራ ነው!ሃይላችሁን ለነገ ቆጥቡት! ምክንያቱም ከ2 ዓመት በሁዋላ ዕቅዱወደ አማራ ክልል ፊቱን አዙሮ አማራን መጨፍጨፍ ነው! እመኑ በእያንዳንዱ የትግሬ ሞት የአማራ ሞት አለ! በእያንዳንዱ አማራ ሞት ውስጥ የትግሬ ሞት አለ! ይህ ፖለቲካ አይደለም! ይህ የፓርቲ ጉዳይ አይደለም! ህዝብ ለህዝብ ቁርሾ ውስጥ ከትቶ አማራን አዳክሞ ትጥቁን አስፈትቶ እርቃኑን ማስቀረትና አጋዥ አልባ አድርጎ በማሽመድመድ ወደ አስቀያሚው የ "ሞጋሳ" ባህል የሚደረግ ጉዞ ነው! ስለዚህ እባካችሁ....!" እያልን ከ2 ዓመት በፊት ተደጋጋሚ ለቅሶ ቀረሽ ጩኸት ጮኸናል!በፊት በዚሁ ገጽ የለጠፍናቸውን ጽሁፎች ደግማችሁ ማየት ትችላላችሁ! ደግማችሁ ማየት ብቻ አይደለም! ልክ እንደ ያኔው ደግማችሁ በኮመንት መሳደብም ትችላላችሁ!
እንደማጠቃለል የአማራ ህዝብ ቁጥር አንድ ጠላት ማነው? ቁጥር ሁለት ጠላት ማነው? ቁጥር ሶስት ጠላትስ? ይህንን ለዩ! እነዚህን ጥያቄዎች በአግባቡ መልሱ! መጀመሪያ በዚህ ተስማሙ! ሌላው ነገር ሁሉ ከዚህ ጥያቄ መመለስ በሁዋላ የሚደርስ ነው::
በዚህ ገጽ ሃሳቦች የምትስማሙ ተከታዮቻችን እነዚህን የቴሌግራም ቻናሎቻችንን ሸር እና ጆይን አድርጉት::

👇👇
https://t.me/devilsgoal

መልካም ጊዜ እንዲመጣ ምኞታችን ነው በሰላም ቆዩን::🙏🙏🙏
Telegram
የሳጥናኤል ጎል በኢትዮጵያ
በዚህ ቻናል በሀገራችን ላይ ስለሚደረጉ የፖለቲካ ሴራዎች 'የሰይጣኒዝም ፍልስፍ እና ሴራወች ይጋለጣሉ ዶክሜንቶች በደንብ ይበረበራሉ! ፈጣሪ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ ይቺ የተቀደሰች ሀገራችንን በቸርነትህ ጠብቃት በምህረትህ አድናት ለጠላቶቿ እጅ አንዳሰጥ አንተ አግዛት ሀሳብ አስተያዬት ካላችሁ 👇 @Tsionitalove አድርሱን
👍106❤37🤔20🥰18
July 12, 2022 14.9K 31