🌼 ‼️ አዲስ ዓመት ማክበር ማለት ! ‼️በፍፁም ንፅህና ታላቅ በዓል አድርገን ልናከብር ይገባናል ! 🌼" የተባረከ የመስከረም ወር የግብፅና የኢትዮጵያ አመታት ወሮች ርእስ ነው፡፡ የቀኑ ሰአትም ከሌሊቱ ሰዓት የተስተከለ ዐሥራ ሁለት ነው፡፡ ከዚህ በኋላ እያነሰ ይሄዳል፡፡ አሁንም በፍፁም ንፅህና ታላቅ በዓል አድርገን ልናከብር ይገባናል፡፡ ይህች እለት ከሌሎች ዕለታት ተለይታ የተባረከች ናትና ከክፉ ስራዎችም ሁሉ ተለይተን እግዚአብሔር ደስ የሚሰኝባቸውን አዳዲስ የሆኑ በጎ ሥራዎችን እንሰራ ዘንድ ይገባናል፡፡ አዲሱ ዘመን የምድርን በረከት የምናገኝበት ወር በመሆኑ ነቢዩ ዳዊት "ወትባርክ አክሊለ አመተ ምህረትከ" ይላል። በቸርነትህ ዘመን የተገኘውን እህሉን ታበዛዋለህ ገበሬው እንደ ዘውድ አድርጎ ያመርተዋልና አክሊል አለው ፤ አንድም በርዕሰ ዕፅ ይገኛልና ፤ አንድም የስንዴ የገብስ ትቱ እንደ ዘውድ ነውና:: ተራሮች ልምላሜን አግኝተው ደስ ይሰኛሉ ፤ የምድረ በዳ ተራሮችም በዝናብ ይረካሉ ፤ ኮረብቶችም ደስ ብሎአቸው ልምላሜውን እንደ ዝናር ይታጠቃሉ ፤ የበግ አውሮች ስብን ይሰባሉ ፤ ሸለቆችም እህልን ተሞልተው በደስታ ያመሰግናሉ ይዘምራሉ ብሏል። [ መዝ.፷፬፥፲፩ ] ሌሊቱ አልፎ ቀኑ ሲተካ ነጋ እንደምንል ክረምቱም አልፎ በጋው [ጠባ] እንላለን። ይህም ከጨለማ ወደ ብርሃን እንደዚሁም ሌሊቱን እንደምን አደራችሁ? በማለትም ሰላምታ እንለዋወጣለን መልሱም እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ነው። ምክንያቱም ግርማ ሌሊቱን አሳልፎ ብርሃነ መዓልቱን እንዳቀዳጀን መዋዕለ ክረምቱንም አሳልፎ ንፁሕ አየርና ሰማይ ለማየት ላበቃን አምላክ ምስጋና ማቅረብ ተገቢ ስለሆነ ነው። መስከረም አሮጌው ዘመን አልፎ አዲሱ "ዘመን የሚተካበት የወሮች መጀመሪያና የምድር ፍሬና የአደይ አበባ መታየት የሚጀምርበት ለፍጥረት ሁሉ አመች የሆነ የደስታ የተስፋና የበረከት ወር ነው:: " ⭕️መርጌታ አይነኩሉ @ayne_kulu 🌼 🕊 🌼
13
8