📌አንዳንድ ነጥቦች…‼️
የፋኖ መሪዎች ጫካ የገቡት ስርዓት ለመትከል ነውና አንበጥብጧቸው!!!
ጥቂት የፌስቡክ አውደልዳዮች የሕዝብን ትግል ለመከፋፈል ብቅ ብቅ እያሉ ነው። እየተካሄደ ያለው የሰፈር ጨዋታ አይደለም፤ የህልውና ትግል እንጅ። አንዳንዱ በግሉ ሲተች እኔ ጎንደሬ ስለሆንኩ ነው፤ እኔ ጎጃሜ ስለሆንኩ ነው እያለ ሲጃጃል እያየን ነው። ይህ ጨዋታ አልፎበታል።
የጎጃም፣ የሸዋ፣ የወሎና የጎንደር የትግል መሪዎች የጋራ ቤታቸውን ለማቆም ዝናብን፣ ብርድንና አገዛዙን ገጥመዋል።
አንተ አንድ ሰው ነህ በቃ! በዛ ላይ ሕዝብ አልወከለህም። እናም ድክመትህም ሆነ ጥንካሬህ የግልህ እንጅ የትውልድ አካባቢህ አይደለም። ጎንደሬ ተተቸ፤ ጎጃሜ ተሰደበ፣ ሸዋ ተገላመጠ፣ ወሎዬ ተንኳሰሰ የምትለው አንተ ማን ሆነህ ነው?
የፋኖ መሪዎች ነፍጥ ይዘው ጫካ የገቡት ሰፈራቸውን ነጻ በማድረግ የጎበዝ አለቃ ለመሆን አይደለም፣ ሀገር ለመረከብ እንጅ!
በመሆኑም በጋራ እየታገሉ ያሉ መሪዎችን አትከፋፍሉ፤ እረፉ‼️
#መውጫ:- ይህ ከአማራነት አንፃር የሚቆረቆሩትንና የሚሞግቱትን አይጨምርም❗️
https://t.me/Mulugetaanberber
Forwarded fromMulugeta Anberber
13August 29, 2024 2.6K