ስለዐማራና ዐማርኛ ጥንታዊነት ‼️
1. የነገስታትና የአማልክት ስሞች
የነገስታት ስሞች፤
በፑንት የንጉሰ ነገስት መንግስት ዘመን ከ2800 ዓ.ዓ ገደማ ጀምሮ የነገሱ የግብጽ ነገስታት ከፑንት ጋር ጥብቅ የንግድ ትስስር ነበራቸው። በዚህም የንግድ ትስስር ከፑንት ከርቤ፣ ቀረፋ፣ ሙጫ እጣን፣ የሰጎን እንቁላልና ላባ፣ የድብ ቆዳ፣ ዝንጀሮ፣ አህያ፣ ኮርማ፣ በሬ፣ የአውራሪስ ቀንድ፣ የወርቅ የብርና የነሃስ እቃዎች እንዲሁም የመድሃኒት እፅዋቶች እና ሌሎችም ነገሮች ጭምር ይላኩ ነበር።
የግብጽ ንግስት የሆነችው ሃትሸፕሱት (1504-1482) 5 የንግድ መርከቦች ወደ ፑንት ልካ የነበረ ሲሆን በአንዱ መርከበኛ ተስሎ በግብጽ በአንድ ቤተ መቅደስ ውስጥ የሚገኘው የስዕል መረጃ፥ ከ1500 ዓ. ዓ ገደማ "ፐረሁ" በተባለ ንጉስና "አጪ/አጢ" በተባለች ንግስት የሚተዳደሩ በእርሻና በንግድ ሙያ የሰለጠኑ፣ በገጠርና በከተማ የሚኖሩ፣ የተፈጥሮ አማልክትና ቤተ መቅደስና ካህናት ያሏቸው ፑንታዊያን ተብለው የሚጠሩ በቀይ ባህር ምዕራባዊ ጠረፍ የሚገኙ ጥንታዊ ሰዎች እንደነበሩ ይገልፃል።
የንግስቷ ስም "አጪ/አጢ" አማረኛ ስለመሆኑ አያጠራጥርም። በዚህ የአማርኛ ስም ላይ የፑንታዊያን መኖሪያ ተብለው የተሳሉት ጎጆ ቤቶች አሰራራቸው አማራ በሚኖርበት በሰሜን ኢትዮጵያ ካሉት ቤቶች ጋር አንድ አይነት ሆነው መገኘታቸው እንዲሁም በግብጽ ከጌቶቻቸው ጋር ከተቀበሩ ዝንጀሮዎች በተወሰዱ የDNA ናሙናዎች ዝንጀሮዎቹ ዝርያቸው አማራ በሚኖርበት በሰሜን ኢትዮጵያ ብቻ የሚገኝ መሆኑ የአማራንና የአማርኛን ጥንታዊነት ያረጋግጣል።
በዳማት የንጉሰ ነገስት መንግስት ዘመን (1000 - 10 ዓ.ም?) የስልጣኔ አሻራዎች ብዙ ሲሆኑ የዳማትን መንግስትና ስልጣኔ የሚመለከቱ የድንጋይ ላይ ጽሁፎች ዋነኛዎች ናቸው። የድንጋይ ላይ ጽሁፎቹም በየሀ፣ መጠራ፣ ከስከሴ፣ ሀውልቲ፣ አዲቀዋህ፣ አዲገለሞ፣ እንዳጭርቆስ ነው የተገኙት። የተገኙት የድንጋይ ላይ ጽሁፎች 13 አጫጭር የነገስታት ዜና መዋዕሎች ሲሆኑ የተፃፉትም በዳማታውያን በራሳቸው ቋንቋና በሳባ ቋንቋ ነው። በዜና መዋዕሎቹ ላይ የነገስታት ስሞች፣ የአማልክት ስሞችና ሌሎችም ነገሮች የሰፈሩ ሲሆን ከሰፈሩት የነገስታት ስሞች መካከል "ለመነ" ይገኝበታል።
ንጉስ ለመነ በዜና መዋዕሉ "የዳማታውያን፣ የሳባውያን፣ የአበራውያን የቀዮችና የጥቁሮች ንጉሥ ሲል ግዛቱ የሚያቅፋቸውን ህዝቦችና የግዛቱን ስፋት ገልጿል። የንጉሱ ስም "ለመነ" አማርኛ ብቻ ነው። ትርጉሙም ግልፅ ነው።
በአክሱም የንጉሰ ነገስት መንግስት ዘመን (10 ዓ.ም - ?) ፤ ከአክሱም ነገስታት መካከል ትንሽ የማይባሉት ስማቸው አማርኛ መሆኑ ነው። አግባ፣ ጉም (ገርስም) ፣ አስጎምጉም፣ ለትም፣ ተላትም፣ አይዙር፣ አስፈሪ፣ ፍሬ ሠናይ፣ አርፍድ፣ ውድም አስፈሪ፣ ግርማ አስፈር፣ ባህር፣ ወሠን ሰገድ፣ ለአብነት ሊጠቀሱ ይችላሉ። እነኝህ ስሞች ደግሞ ቅልብጭ ያለ ትርጉም ያላቸው አማርኛ ቃላት ናቸው።
የአማልክት ስሞ፤
በድንጋይ ላይ ተፅፈው በተገኙ የዳማታ ነገስታት 13 አጫጭር ዜና መዋዕሎች ላይ ከተጠቀሱት ብሔራዊ አማልክት ስሞች መካከል "ሸመነ" ይገኝበታል። "ሸመነ" ደግሞ አማርኛ ነው። ትርጉሙም ግልፅ ነው።
የጽሁፍ መረጃ፤
ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ200 - 130 ዓ.ዓ ባለው ጊዜ ከውስጥ በሰሜን ኢትዮጵያ የሚኖሩ ህዝቦች የሚናገሩት አማርኛ የሚባል ቋንቋ እንደነበረ ድርሳን ላይ የተፃፈ መሆኑ።
በአክሱም የንጉሰ ነገስት መንግስት ዘመን የሕዝቡ የዕለት ከዕለት ቋንቋ ከመሆን አልፎ ሠራዊቱና መኳንንቱ በግዕዝና አማርኛ ይገለገሉ የነበረ መሆኑ ። በአክሱም የንጉሰ ነገስት መንግስት ዘመን፥ አክሱማውያን ማለትም የግዙፉ የአክሱም አውራጃ ነዋሪዎች የአማርኛ ተናጋሪዎች ስለመሆናቸውና አውራጃው ርስታቸው መሆኑ። ዘራቸው ከቤጃ ዘላኖች የሆኑት "ነገደ ትግረ" የአክሱምን መንግስት ወርረው ከመዲናው ስለማባረራቸው እና በዚህ ጊዜ ትግርኛና "ነገደ ትግሬ" ስለመፈጠሩ። ይህም ማለት ትግርኛም ሆነ ነገደ ትግሬ ከ8ኛው ክፍለ ዘመን በኋላ ነው የተፈጠረው።
የአርኪኦሎጅ መረጃ፤ የስነ ልሳን ባለሙያው አምሳሉ ጥንታዊ የድንጋይ ላይ ጽሁፎች ስለመገኘታቸው አብራርቷል።
መደምደሚያ፦ አማራ የፑንት፣ የዳማት፣ የአክሱም፣ የአዳፋ፣ የሸዋ፣ የደዋሮ፣ የወጅ፣ የበጌምድርና እንደገና ድጋሚ ወደሸዋ የተመለሰው የሸዋ የንጉሰ ነገስት መንግስት ባለቤት የሆነ ባለደማቅ ታሪክ ህዝብ ሲሆን አማርኛም ከ5-6 ሺህ ዓመታትን ያስቆጠረ የዳበረ ቋንቋ ነው።
ከየትኛውም ወገን ይሁን በዐማራና በዐማራነት ላይ የሚቀልድ፣ ትርክትና ታሪክ የሚያጣምም ግለሰብም ዬሁን ቡድን ለፍርድ መቅረብ ይኖርበታል። በተለይም በዐማራ የብሔርተኝነት ትግል ውስጥ በፋኖ መዋቅር ከፍተኛ አመራር ሁኖ እንደ የቆዬ ሞላ አይነቱ ላይ ተገቢውን እርምትና ማስተካከያ መውሰድ ያስፈልጋል።
ዋቢ መጽሐፍት (References)
1. Sergew H. Selassie, Ancient and Medieval Ethiopian History to 1270, 1972, pp. 22-23.
2. J. Doresse, Histoire Sommaire de la Corne Orientale de L Afrique, pp. 47-56; Pankrust, Economic history, pp. 5-6.
3. Ibid, Inscriptions Sudarabiques, pp. 387 - 389.
4. ተክለ ፃድቅ መኩሪያ፣ ኑቢያ-አክሱም-ዛጉዬ
5. Agatarcus (Ago), Pen tes Eryth - as thalasses (on the Erythraean sea)
6. ፈለቀ ገርማሚ፡ ባሻህ ውረድ፡ ገለበው ሰንጎጎ፣ የትግሬ-ቤጃ ማንነት፣ ገ. 5-6።
7. ዶ/ር ፈለቀ ገርማሚ: አቶ ባሻህ ውረድ: አቶ ገለበው ሰንገጎ፣ የትግሬ ቤጃ ማንነት፣ ገጽ. 7 እና 9።
8.ዶ /ር ምስጋናው ታደሰ፣ ከቤተ አማራ እስከ ወሎ
https://www.facebook.com/Amharanism2514
2February 6, 2025 411