"እባቡ የማይተነፍስበት ክልል ውስጥ ገብተናል" 🐸❌
በበረራ ላይ እያሉ ሆስተሷ አውሮፕላን ውስጥ እባብ አይታ በጣም ደነገጠችና እየጮኸች አብራሪው ጋር ገብታ እባብ አውሮፕላን ውስጥ ገብቷል አለችው።
እሱም ችግር የለውም ተረጋጊ አለና የሚበርበትን ጫማ ከፍታ ጨመረና አሁን ሄደሽ እይ አላት።
እሷም ሄዳ ስታይ እባቡ ሞቷል።
ወደ አብራሪው ተመለሰችና እንዴት ሊሆን ቻለ ስትለው እባቡ የማይተነፍስበት ክልል ውስጥ ገብተናል አላት።
😇
የነገሩ ማጠንጠኛ፦ በገጠመህ ሁሉ አትደንግጥ ለሁሉም ነገር መልስ አትስጥ ዝምብለህ ጉዞህን ቀጥልና ጠላትህን የሚያስጨንቅ ከፍታ ላይ ውጣ። 💪
https://t.me/bedru511111
July 5, 2025 4.5K 20 12