አንድ ትልቅ የንግድ መርከብ ተበላሽቶ ቆመ ብዙ መካኒኮች ቢሞክሩትም መጠገን አቃታቸው ፣ በኋላም አንድ የ40… — ኡስታዝ በድሩ ሁሴን bedru husen — TG.ME

አንድ ትልቅ የንግድ መርከብ ተበላሽቶ ቆመ ብዙ መካኒኮች ቢሞክሩትም መጠገን አቃታቸው ፣ በኋላም አንድ የ40 ዓመት ጎልማሳ የመርከብ ኢንጅነር አግኝተው መርከቡን እንዲሰራላቸው ጠየቁት ።

ኢንጅነሩም እሺ ይልና የመርከቡን የተበላሸውን ክፍል ለመለየት ሞተሩን ከታች እስከላይ ከገመገመ በኋላ፣ አነስ ያለች የእቃ ቦርሳውን ከፍቶ ትንሽዬ መዶሻ አወጣና፣ በመዶሻው አንዷን ቦታ መታ፣መታ አረገ ከዚያም ሞተሩ መስራት ጀመረ።

ስራውን እንደጨረሰም የሰራበትን ዋጋ አንድ ሚሊዮን ብር ጠየቀ ።

ባለቤቱ በድንጋጤ ጭንቅላቱን ይዞ "ምን"? አለ ከዚያም ለመሆኑ በዚች ሰኮንድ ውስጥ ምን ሰርተህ ነው ይሄን ያህል ብር የምትጠይቀኝ ? በል ምን እንደሰራህ ዝርዝሩን ጽፈህ ስጠኝ አለው በንዴት።

ኢንጂነሩም በጠየቀው መሰረት በብጣሽ ወረቀት የሚከተለውን ፅፎ ሰጠው ፅሁፉም እንዲህ ይላል

በመዶሻ የመታሁበት 200 ብር
የተበላሸበትን ቦታ ላወኩበት 999800 አለው።

ይሄን ስራ በሰኮንድ ውስጥ ነው የሰራውት ላለፉት 20 አመታት እንዴት በ ሰኮንድ ውስጥ እና በ ደቂቃዎች ውስጥ መስራት እንዳለብኝ ተምሬ ነው፣ ይሄን የማስከፍልህ ለተማርኩበት አመታት እንጂ ለሰራውበት ሰኮን ወይም ደቂቃ አይደለም አለው ይባላል።


https://t.me/bedru511111
April 1, 2025 5K 2 8