ድንቅ ታሪክ
ነብዩላሂ ሙሳ አላህን ያናገሩ ነብይ ናቸው፡፡
አንድ ጊዜ አላህን የጀነት ጎደኛዬን አሳየኝ ብለው ጠየቁ ፡፡
አላህም ወደ አንድ ደካማ ቤት እንዲሄድ የመንገዱን አቅጣጫ ነግራቸው ሄዱ፡፡
የተባሉት ቤት ደርሰው አንኳክተው ገቡና ቁጭ አሉ፡፡
በእድሜ የገፉ እናትና አባቱን የሚካድም አንድ ወጣት ልጅ ተመለከቱ፡፡
ልጁ ሽማግሌዎቹን በመካደም ተጠምዶዋል ያጎርሳቸዋል ያጠጣቸዋል፡፡
በዚህ የተነሳ ቤቱ ማን እንደገባ እንኳን አላወቀም፡፡
ከጨረሰ በኃላም ዞር ብሎ ሲመለከት አንተ እንግዳ ቤት በኩል ገባህ አላቸው?
ነብዩላሂ ሙሳ (ዐ.ሰ) አፉ በለኝ ይሉትና
ልጁም እንዲህ አላቸው
እነሱን እየካደምኩ ስለነበረ በዛ ምክንያት ነው ። ስትገባም ያለየሁክ አላቸው።
ነብይ መሆናቸውን አላወቃቸውም፡፡ ልጁም እንግዳዬ ነህ እሺ ምን ላድርግልህ ከነሱ የተረፈ አለ ትበላለህ አላቸው፡፡
( ነብዩላሂ ሙሳም( ዐ.ሰ) ምንም አልፈልግም ሸኘኝ በቃ አሉት፡፡
ወጪ ከወጡ በኃላም ነብዩላሂ ሙሳም(ዐ.ሰ) ልጁን ጠየቁት እነዛ ሽማግሌዎች ምንህ ናቸው አሉት?
ልጁም ወላጆቼ ናቸው አላቸው፡፡
ነብዩላሂ ሙሳም( ዐ.ሰ) ምንም ሌላ ልጆች የላቸውም ቤተሰብም የላቸውም አሉት፡፡ ልጁም አዎ እኔ ብቻ ነኝ ያለሁት አላቸው፡፡
ነብዩላሂ ሙሳም( ዐ.ሰ) ምንድን ነው የምትሰራው አሉት?
ልጁም ተሸካሚ ነኝ ተሸክሜ ባገኝሁት ብር እነሱን ቁርስ፣ምሳ፣እራት ሳላሳልፍባቸው እየገዛሁ እካድማቸዋለሁ አላቸው፡፡
ነብዩላሂ ሙሳም( ዐ.ሰ) ወላጆችህ ስታስደስታቸው ምን እያሉ ነው ሚመርቁህ አሉት፡፡
ልጁም አይ እሱስ ከባድ ነው የማለገኝውን ነው የሚመርቁኝ በተለይ እናቴ አንድ ነብይ አለ ደረጃህን በጀነት ከነብዩ ሙሳ ጋር ያድርግልህ ትለኛለች፡፡ ስለምትወደው ነው እንጂ እኔ እንኳን ከነሱ እኩል መሆን አልችልም አላቸው፡፡
ነብዩላሂ ሙሳም( ዐ.ሰ)
ታውቀዋለህ ግን ነብዩላሂ ሙሳን አሉት?
አላውቀውም!
እንዳለ እሰማለሁ እንጂ አላቸው፡፡
ነብዩላሂ ሙሳም (ዐ.ሰ) በል እንግዲህ እኔ ነብዩላሂ ሙሳ ነኝ
እኔም የጀነት ጎደኛህ ነኝ አላህን
የጀነት ጎደኛዬን ማን እንደሆነ አሳየኝ ብዬው ነው!
ዛሬ አንተ መሆንህን ያሳየኝ አሉት።
https://t.me/bedru511111
March 9, 2025 3.7K 4 22