በርግጥ አንዳንድ ወንዶች ፌሚኒዝምን የሚደግፉት ሴትን እንደነፃ ሰብዓዊ ፍጡር ስለሚመለከቷት ነው፤ ሌሎች በተቃራኒው ፌሚኒዝምን የራሳቸውን ማህበራዊ ምስል ለመገንባት ይጠቀሙበታል። የመጀመሪያው ሰውዬ ለአንድ መርህ የቆመ ነው፤ ሁለተኛው ሰው ግን በመርሁ በኩል ራሱን የሚሸጥ asshole ነው። አንደኛው «ይህ ትክክል ስለሆነ እደግፈዋለሁ» ይላል፤ ሌላውኛው በተቃራኒው «ይህን ብናገር እኮ እኔን እንደ ጥሩ፣ እንደ ዘመናዊ እና ሴቶችን የሚያከብር ወንድ እንድታይ ያደርገኛል» ብሎ የሚያስብ ዘገምት ነው። ልዩነታቸው በቃላቱ ላይ ሳይሆን በዓላማቸው ላይ ነው።
ይህን አካሄድ በሳይኮሎጂው «validation seeking እና impression management» ይባላል። ሰውየው በውስጡ የሚሰማው የራስ ዋጋ በቂ እንዳልሆነ ስለሚሰማው ከሌሎች አድናቆት ለመሰብሰብ ይጋጋጣል። በዚህ ምክንያት «Nice guy» ወይም ጥሩ ሰው መሆን ለእሱ ከውስጡ የሚጣ ሳይሆን እንደ social currency ከውጭ የሚቀበለው ማንነት አድርጎ ይወስደዋል። ለዛም ነው ሴቶችን ሲያወድስ እና ስለእኩልነት ሲያወራ ስንመለከተው ሞራሊዝምን አክብሮ ሳይሆን፤ ያን ስነምግባር ሲፈጽም በሌሎች ዓይን የሚሰጠውን ዋጋ ቀመር ውስጥ የሚያስገባ እንጭጭ መሆኑን የምነግራችሁ!።
እንዲህ አይነቶችሁ ወንዶች ሃላል ሴቶችን ከሚተቹት በላይ ጨለምተኛ አስተሳሰብ የታቀፉ instrumentalization ባለቤት ወይም ባልቴት ናቸው። instrumentalization ማለት ዋጋን እንደ መጨረሻ ግብ ከመከተል ይልቅ ሌላ ነገር ለማግኘት በእሱ መጠቀሚያ የሚደርጉ እንቁሊጥያሞች ስብስብ ነው። እንዲህ አይነት ወንዶች ሴቷን የእራሷ መብት ያላት ሰው ሳይሆን የራሳቸው self-image የምታረጋግጥ መስታወት ነው የሚያደርጓት።
ብዙ ግዜ እሰማቸዋለሁ። በአፋቸው «ሴቶች ነፃ መሆን አለባቸው» ይላሉ፤ ነገር ግን በውስጣቸው የሚፈልጉት የሆነች ሻፉ ያሉባት ሴት እነሱን እንደምርጥ ወንድ ተመልክታ እንድትመርጣቸው ነው። የሚገርመው ደግሞ እንዲህ አይነት ወንድ ሴቷ ከእሱ በላይ ነፃ መሆኗን ሲመለከት የሌለ የበታችነት ስሜት ነው የሚሰማው። እኩልነት ብሎም የሚያወራለት አይዶሎጂ የሴቷን ነፃነት በማሰብ ሳይሆን የራሱን ምስል ለማረጋገጥ የሄደው እርቀት ነው። ይህ covert contract የሚባል የስነልቦና ሆነ የስነ መታወክም ምልክት ነው!። እንዲህ አይነቱን ወንድ አዕምሮውን በቪድ በርግደን ብናየው እንዲህ የሚል ድምፅ አለው፦«እኔ ላንቺ ጥሩ እሆናለሁ፤ አንቺም በምላሹ እምስሽን ትሰጪኛለሽ።» የሚል ድብቅ አላማ ያነገተ ላም አለኝ በሰማኝ ጡታ ግን ደርቋል 😂 ነገር ግን ስማኝ ወዳጄ ፍቅር ለሞራላዊ ባህሪ የሚከፈል ደመወዝ አይሆንም፤ ሌላ ሰውን ማክበርም የሌላውን ሰው ፍቅር ለመግዛት የሚሰጥ ተመን አይደለም።
ስለዚህ ምክሬን ስማ። ይህ Nice guy ለመሆን የምትጋጋጠው ነገር ውጤቱ ደም በደም ሆኖ መቅረት ብቻ ነው። በመጨረሻም የሌለ ወይም የትዬለሌ ስትጎዳ ውስጥ የሚቀረው ጥያቄ ይህ ብቻ ነው፦«እኔ ይሄ ሁሉ ነገር አድርጌላት እሷን ግን ግድ አልሰጣትም!»።
እዚህ ጋር ነው የተደበቀው ጥላህ አፈትልኮ የሚወጣው። አንተ ያደረገከው መልካምነት በእውነት ከልብ የመጣ ቢሆን ኖሮ ከእሷ ምላሽ አለማግኘት የሞራሉን ዋጋ ባላሳነሰው ነበር። ነገር ግን ምላሽ አለማግኘትህ ቁጣ ከፈጠረብህ፤ ያ መልካምነት ከአላምህ ይልቅ ኢንቨስትመንት ነው። ወዳጄ ይህ moral grandstanding ጭምር ነው። ሰው ሞራላዊ አቋሙን ለአላማው ትግል ከማዋል ይልቅ ራሱን እንደ ሞራላዊ ሰው ለማሳየት ሲጠቀምበት የሚፈጠር ሰልፊሽነት!።ሁሌ ቢሆን እንዲህ አይነት ወንድ ስለ ሴቶች መብት ይሰብካል፣ ስለ toxic masculinity ይተቻል፣ ስለ patriarchy ይናገራል፣ የናዋል ኢል ሳዳዊ እና የሲሞን ዴ ቤውቬር አባባሎችን በቃሉ ይሸመድዳል። እንዲህ ማድረጉ እኮ ችግር የለውም። ነገር ግን የሚናገረው ዕውን ስለሚያምንበት ነው? ወይስ ሰዎች እንደዛ አድርገው እንዲያስቡት ስፈለገ ነው?። በርግጥ ይህ ውስጣዊ ግጭት የሚፈጥር የተሳሳተ አካሄድ ነው። አንድ ሰው ራሱን እንደ ጥሩ ሰው ለማየት ሲፈልግ እና ያ ጥሩ ሰው መሆኑን ግን ማረጋገጥ የሚፈልገው ከውጭ ሰው ሲሆን የሚፈጠር cognitive dissonance ግጭት ነው።
ከዚህ ግጭት በኋላ አዕምሮ እውነቱን ከመቀበል ይልቅ ለራሱ የሚያጽናና ታሪክ ይፈጥራል። እነዚህ የውሸት ትርክቶች ደግሞ ወደለየት አጥፊ የሚቀይሩ አስፈሪ አስተሳሰቦች ናቸው። «ጥሩ ወንድ ነህ» መባሉትን ከውጭ ማግኘት ስለቸገረው በውስጡ self-deception ለእራሱ መልሶ መናገር ይጀምራል። በስራው ውጤት ሌሎች ሰዎችን ከማሳመን ይልቅ እራስን ማታለል ቀላሉ መንገድ ነው የሚባለው ከዚህ አንፃር ነው። ቢሆንም አንዳንዴ ሰውየው ራሱን እየጠቀመ መሆኑን እንኳ ሳያውቅ ሞራሊቲን ለራሱ ጥቅም ሊያውል የሚችልበት አድቫንቴጅም አለ። ሴቶችን እየተከላከለ መስሎት ሊሆን ይችላል፤ በእውነቱ ግን የሚፈልገውን በውስጡ የሚጮኸው ድምፅ «ጥሩ ወንድ ነህ» ወደሚል ንግግር የመቀየር ፍላጎት ነው።
በመጨረሻም የሞራሊቲ እውነተኛ ፈተና በሰዎች ፊት የሚረጋገጥ ማስረጃ ሳይሆን፤ ማንም ሳያየን የምናደርገው የውስጥ ድምፅ ነው። ማንም ባያመሰግንህ አቋምህን ትጠብቃለ፤ ማንም ባይወድህም መንገድህን በፀጥታ ትከተላለህ። ያኔ ነው ዋጋ ያለው ሰው ወይም ዋጋ ያለው ወንድ የምትሆነው!። ነገር ግን ሞራሊዝምን የምትከተለው በሌሎች ዘንድ ሽልማት ለማግኘት ከሆነ ይህ ሞራሊቲ ስትራቴጂ ብቻ ሳይሆን ደናቁርትነት ጭምር ነው። ይህ ኢድየትነት ነው፣ ይህ ቫፊንኩሎ መሆን ነው ይህ ቢችአስ መሆንንም ያካትታል!።እኔም ለዛ ሽልጥልጥ ወንድ ጥያቄ ብቻ ነበር ያቀረብኩለት፦አንተ በእውነት ለሴቶች እኩልነት ለመቆም አስበ ነው ወይስ እኩልነትን በመጠቀም ከሴቶች ፑሲ ለማግኘት የሄድከው እርቀት ነው?። ምክንያቱም አንድ ሰው ሴቷን ነፃ እንድትሆን እየሰበከ በውስጡ ግን እሷ እሱን እንድትመርጥ የሚጠብቅ ከሆነ፤ ይህ እኩልነት ሳይሆን የሴት ገላ ጥምዓት ነው!።
ጀለስ እንደዛ ወንድ ሲያበሻቅጥ የፌሚኒዝምን አይዶሎጂ እየደገፈ አለመሆኑ ገብቶኛል፤ ይልቅስ ዕድል እንዲሰጠው እየጠበቀ ነበር። እደሉም በአፉ፦«እኔ ከሴቶች ጎን ነኝ» ይላል፤ በውስጥ ደግሞ «እቺን ልጅ መቼ ይሆን የምተኛት?» የሚል ኤስቱፒዶ ቶንቶ ወይም የወንድ ደናቁርት መገለጫ ነው!።@Armemo_offical




