በኢትዮጵያ እና በሌሎች 74 ሀገራት ላይ ተጥሎ የነበረው የጉዞ እገዳ በፌዴራል ፍርድ ቤት ተነሳ!
በኒውዮርክ የሚገኘው የፌዴራል ፍርድ ቤት፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ በ75 ሀገራት ላይ ተጥሎ የነበረውን የኢሚግራንት የቪዛ እና የጉዞ እገዳ ውድቅ በማድረግ አንስቶታል።
* ፍርድ ቤቱ የተጣለው እገዳ ህጋዊ መስፈርቶችን አያሟላም በሚል ሙሉ በሙሉ እንዲነሳ ወስኗል።
የመንግስት ቀጣይ እርምጃ፡ የአሜሪካ መንግስት (የሀገር ውስጥ ደህንነት መሪያ) በፍርድ ቤቱ ውሳኔ ላይ ይግባኝ ካላቀረበ፣ ውሳኔው ወዲያውኑ ጸንቶ ስራ ላይ ይውላል።
ለኢትዮጵያውያን ያለው ትርጉም፡ መንግስት ይግባኝ ካላለ፣ በሂደት ላይ የነበሩ እንዲሁም አዲስ የሚጠየቁ የኢሚግራንት (የቋሚ ነዋሪነት) ቪዛ ማመልከቻዎች እንደገና መስተናገድ ይጀምራሉ፤ ዜጎችም በቪዛ ወደ አሜሪካ መግባት ይችላሉ።
ተስፋ ሰጭ ዕድል፡ ይህ ውሳኔ ከቤተሰብ ጋር ለመቀላቀል እና በቋሚነት ወደ አሜሪካ ለመጓዝ ሂደታቸው ተደናቅፎ ለቆየ በርካታ ኢትዮጵያውያን ትልቅ ተስፋ እና አዲስ በር የሚከፍት ነው።
ሂደቱን በተመለከተ የሚወጡ አዳዲስ የህግ እና የይግባኝ መረጃዎችን በትኩረት መከታተል አስፈላጊ ይሆናል።
አልፍሬዶ አድቫይዘሪ – ለአእምሮዎ እረፍት፣ ለጉዞዎ ብርሃን




