የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞች ማረጋገጫ (Verification) መመሪያ:-
📌ይህ ሰነድ የማረጋገጫ ሂደቱ ስልታዊ እና ቀልጣፋ በሆነ መንገድ እንዲከናወን የሚረዱ ሶስት ዋና ዋና ክፍሎችን ይዟል።
📋 ክፍል 1፡ የግድ መሟላት ያለባቸው ሰነዶች (11 ዓይነቶች)
ለእያንዳንዱ ሰራተኛ ሊሟሉ የሚገባቸው መሰረታዊ የሰው ኃይል መረጃዎች፦
📌ብሄራዊ መታወቂያ፡ ከተመዘገበበት ስልክ ቁጥር ጋር።
📌የቢሮ መታወቂያ፡ ወቅታዊ የሆነ።
📌የቅጥር ደብዳቤ፡ የመጀመሪያ ቅጥር ሰነድ።
📌የዝውውር ሰነድ፡ ከሌላ መሥሪያ ቤት የመጡ ከሆነ።
📌የደረጃ እድገት፡ የተሰጡ የደረጃ እድገት ደብዳቤዎች።
📌የአገልግሎት ማራዘሚያ፡ ጡረታ ወጥተው ለሚሰሩ ብቻ።
📌የትምህርት ማስረጃዎች፡ ሁሉም የትምህርት ደረጃዎች።
📌የጡረታ ፎርም፡ የተሞላ የጡረታ መረጃ።
📌የስራ ልምድ፡ የቀድሞ የስራ ልምድ ማስረጃዎች።
📌የሹመት ደብዳቤ፡ ተሿሚ ለሆኑ አመራሮች።
📌የድልድል/ምደባ ደብዳቤ፡ አዲስ ድልድል ተደርጎ ከሆነ።
💢ክፍል 2፡ ተጨማሪ የማህበራዊ ሁኔታ ሰነዶች
📌የጋብቻ ሰርተፍኬት
📌የልጆች የልደት ሰርተፍኬት (ልጆች ካሉ)
⚙️ ክፍል 3፡ የአሰራር ቅደም ተከተልና መመሪያዎች
✍ሂደቱ ያለምንም መስተጓጎል እንዲሄድ ተቋማት የሚከተሉትን ተግባራት ማከናወን ይኖርባቸዋል፦
📌መርሃ-ግብር ማዘጋጀት፡ በቀን ለአንድ መረጃ ሰብሳቢ 7 ሰራተኞችን በማደራጀት ቀኑን አስቀድሞ ማሳወቅ።
📌የአካል መገኘት፡ በወሊድ፣ በህመም ወይም በአመት እረፍት ላይ ያሉ ሰራተኞች በአካል ቀርበው መመዝገብ አለባቸው።
📌የሰው ኃይል መመደብ፡ ስራውን የሚከታተል፣ ጥንቃቄ ያለውና የIT እውቀት ያለው ኃላፊ መመደብ።
📌 መረጃዎችን - በጊዜ፣ በጥራትና በማደራጀት የዲጅታል ሲቪል ሰርቪስ ግንባታን ለማሳካት የድርሻቸውን እንወጣ። መልዕክታችን ነው።
💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
ክቡር አቶ መንግስቱ ማትወስ
የሲዳማ ብ/ክ/መ ሲቪል ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ ሀላፊ
ወቅታዊ ትኩስ እና የተሟላ መረጃ ለማግኜት
website: http://www.sidamapublic.gov.et
Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=100064754288699
Telegram: https://t.me/sidamaregionpublicsevicebureau
WhatsApp: https://chat.whatsapp.com/BoWQdQnsIugDADhj4svuEP
Youtube: https://www.youtube.com/@DagitteOwaantewebsite:












