ከቴምብር ቀረጥ ነጻ የሆኑ 👉 በመንግሥት በጀት የሚተዳደሩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች፤ 👉 የአስመጪነት ፈቃድ… — አለ ሕግ — TG.ME

ከቴምብር ቀረጥ ነጻ የሆኑ
👉 በመንግሥት በጀት የሚተዳደሩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች፤
👉 የአስመጪነት ፈቃድ ያላቸው ነጋዴዎች ለሽያጭ የሚያስመጡት ንብረት በአስመጪዎቹ ስም ሲመዘገብ፤
👉 መንግሥት ባጸደቃቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች እና ኮንቬንሽኖች መሠረት ሰነዶች ነጻ ሊደረጉ ይችላሉ፤
👉 ተመሳሳይ መብት የተሰጠ መሆኑ ሲረጋገጥ ገንዘብ ሚኒስቴር ኢምባሲዎችን፣ ቆንስላዎችን እና ዲፕሎማቲክ ሚሲዮኖችን ከቴምብር ቀረጥ ነጻ ሊያደርጋቸው ይችላል፤
👉 የአክሲዮን ድርሻ የምስክር ወረቀት ሲመዘገብ፤
👉 ለኢንቨስትመንት በሚወሰድ ብድር የመያዣ ሰነድ፤
👉 አዲስ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ሥራ አክሲዮን ማህበር ለጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞቹ በዱቤ ግዥ የሚያቀርባቸው የካፒታል ንብረቶች በስሙ ሲመዘገብ፤
👉 በኤክስፖርት ንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶች ለሥራ ማስከጃ ከሚወስዱት ብድር ጋር ተያይዞ የሚገኝ የመያዣ ሰነድ፤
👉 የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን ሴቶች በገቢ ምንጭነት እንዲጠቀሙባቸው ከመንግሥት የተሰጡት ተሸከሪካሪዎች የባለቤትነት ስም ዝውውር ሰነድ፤
👉 የግብርና ምርት ማሳደጊያዎች አቅራቢ ድርጅት የማዳበሪያ አቅርቦት ለአርሶ አደር ለማደል ከሚወስደው ሜርቸንዳይዝድ ብደር ጋር በተገናኘ የመያዣ ሰነድ፤
👉 የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለኢንተርፕራይዞች ለሊዝ ፋይናንስንግ ሥርዓት የሚያቀርባቸው ተሽከሪካሪዎች በባንኩ ንብረት ባለቤትነት ስም ማስመዝገቢያ፡፡
በታክስ ጉዳዮች ትምህርት ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
❤1👍1
August 20, 2026 3.9K 31