የተሻሻለው አዋጅ ስለታክስ ማጭበርበር ምን ይላል? ነሐሴ 20/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር) በተሻሻለው… — አለ ሕግ — TG.ME

የተሻሻለው አዋጅ ስለታክስ ማጭበርበር ምን ይላል?
ነሐሴ 20/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)
በተሻሻለው የፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1434/2018 መሰረት “የታክስ ማጭበርበር” ማለት ታክስን ለመሰወር ወይም ህጋዊ ያልሆነ የታክስ ጥቅም ለማግኘት ሲባል የሚከተሉትን ድርጊቶች መፈጸም ነው፤
👉 ሐሰተኛ የሂሳብ መዝገቦችን፣ ሰነዶችን፣ ደረሰኞችን ወይም ሌሎች ሰነዶችን ማቅረብ፣
👉 ገቢን፣ ግብይትን ወይም ታክስ የሚከፈልበትን እንቅስቃሴ መደበቅ፣
👉 ሐሰተኛ ደረሰኞችን ማዘጋጀት ወይም መጠቀም፣
👉 ሐሰተኛ የታክስ ማስታወቂያ ማቅረብ
👉 ሰነዶችን ማጥፋት፣ መቀየር፣ መደበቅ፣
👉 ከአንድ በላይ ወይም ትይዩ የሂሳብ መዛግብትን ወይም ሰነዶችን ማዘጋጀትና መያዝ፣ እንዲሁም ለታክስ ባለስልጣኑና ለሌሎች አካላት ማቅረብ፤
👉ሐሰተኛ የተቀናሽ ወጪዎችን፣ የግብር ወይም የታክስ ነፃ መብት፣ የተመላሽን ወይም የማካካሻ ጥያቄን ማቅረብ፤
👉 ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ የታክስ ግዴታን ለመቀነስ ማናቸውንም ሌሎች ድርጊቶች መፈጸም ወይም ሕግ እንዲፈፅሙ የሚያስገድዳቸውን አለመፈጸም፡፡
በአዋጁ የተሻሻሉ የታክስ ስሌቶች እና የይርጋ ጊዜ ገደብን በተመለከተ ሲገልጽ የታክስ ባለስልጣኑ የማጭበርበር ድርጊት የተፈጸመ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ያገኘ እንደሆነ የራስ ታክስ ስሌት ማስታወቂያውን ካቀረበበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 10 (አስር) ዓመት ውስጥ ሊያሻሽል ይችላል ይላል፡፡
ይሁን እንጂ በአዋጁ ንዑስ አንቀጽ 5 ላይ የታክስ ማጭበርበር ድርጊት መፈጸሙ በማስረጃ የተረጋገጠ በሚሆንበት ጊዜ የታክሱ ባለስልጣን የ10 (አስር) ዓመቱን የይርጋ ጊዜ ገደብ ሳያልፍ በማናቸውም ጊዜ የታክስ ውሳኔ ማሻሻያን ሊያደርግ እንደሚችል ይገልጻል፡፡
❤8
August 26, 2026 3.2K 27