የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪን ይመለከታል
ለኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያዎች ማኅበር አባላት፡
ቀደም ሲል በተላለፈው ጥሪ መሰረት የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያዎች ማኅበር የ2018 በጀት ዓመት መደበኛ የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ቅዳሜ ነሀሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ ሜክሲኮ ሰንጋተራ አካባቢ በሚገኘው የኅብረት ባንክ ዋና ህንጻ (ህብረት ታወር) አዳራሽ ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ እንደሚካሄድ እየገለጽን ለዝግጅት እንዲመቸን በጉባኤው የምትገኙ መሆኑን በኢሜል አድራሻችን [email protected] ስልካችሁን በመጻፍ እንድትመዘገቡ በማክበር እንጠይቃለን፡፡
የአባልነት ክፍያ ያላጠናቀቃችሁአባላት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000540887091 ገቢ በማድረግ የከፈላችሁበትን ደረሰኝ በኢሜል መላክ ትችላላችሁ።
የጉባኤው ረቂቅ አጀንዳዎች፡
1. የ2018 በጀት ዓመት የማኅበሩን የስራ ክንውንና የውጭ ኦዲተር ሪፖርት መርምሮ ማጽደቅ፤
2. የማኅበሩን የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ተወያይቶ መወሰን፤
3. ለማኅበሩ በጎ ፈቃደኛ ባለውለታዎች የእውቅና አሰጣጥ ስነ-ስርዓት ማካሄድና ሌሎችም ናቸው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-553-01-22 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
ኅብረት ባንክ ለማኅበራችን ለሚያደርገው የተለመደ ትብብር ከፍተኛ ምስጋናችንን እናቀርባለን።
ከሰላምታ ጋር
የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያዎች ማኅበር (ELA)
11August 30, 2026 1.8K 3