የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት የውክልና አገልግሎቱን በአምስት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ከወረቀት ነጻ በሆነ ሲስተም ተደራሽ ማድረግ መጀመሩን አሳውቋል።
ሜክሲኮ በሚገኘው ቅርንጫፍ አስር ልዩ እና መደበኛው ቅርንጫፍ ፣አያት አደባባይ ሎሚያድ ሱፐርማርኬት በሚገኘው ቅርንጫፍ አስራአንድ እንዲሁም ካዛንቺስ እናት ታወር ላይ በሚገኘው ቅርንጫፍ ስምንት እና ቦሌ በሚገኘው ቅርንጫፍ አስራሁለት ጽ/ቤቶች ነው አገልግሎቱን መስጠት የተጀመረው።
በቅርቡም በሁሉም ቅርጫፎች ተግባራዊ ለማድረግ እየሰራሁ እገኛለሁ ሲል የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት አስታውቋል።
ከተገልጋዮች ምን ይጠበቃል ?
የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት ከወረቀትአልባ አገልግሎት በተጨማሪ በቴሌሳይን መተግበሪያ አማካይነት የቤተሰብ የጠበቃ እና የአስተዳደር ውክልና አገልግሎት ወደተቋም መምጣት ሳይጠበቅባቸው ካሉበት ሆነው ማግኘት የሚያስችላቸው አሰራር መተግበሩን አስታውሷል።
@TikvahethMagazine


