የኮማንዶ ክፍለ ጦሩ ዝግጁ መሆኑን የክፍለ ጦሩ አዛዥ አስታወቁ ሐሙስ፣ ነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ.ም… — Addis Maleda - አዲስ ማለዳ — TG.ME

Addis Maleda - አዲስ ማለዳPhoto
የኮማንዶ ክፍለ ጦሩ ዝግጁ መሆኑን የክፍለ ጦሩ አዛዥ አስታወቁ

ሐሙስ፣ ነሐሴ 28  ቀን 2018 ዓ.ም (#አዲስ_ማለዳ)

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የኮማንዶ ክፍለ ጦር በማንኛውም ጊዜ የሚሰጠውን ግዳጅ ለመፈፀም ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ።

የኮማንዶ ክፍለ ጦር አዛዥ የሆኑት ኮሎኔል ሰለሞን ፀጋዬ እንደተናገሩት ከሆነ ክፍለ ጦሩ በቅርቡ “የጥፋት ኃይሎችን በመመንጠር ታላቅ ድል” አስመዝግቧል ብለዋል።

አክለውም የሀገርን ሰላምና ሉዓላዊነት ለማስከበር ያለውን ፅናት ያሳየበት ነው ያሉ ሲሆን ይህም ውጤት “ወታደራዊ ግዳጅን በስኬት መወጣት ብቻ ሳይሆን፣ የአባላቱን የላቀ የውጊያ ጥበብ” በሚገባ ያሳየ ነው ማለታቸውን፣ የመከላከያ ሰራዊት ያጋራው መረጃ ያመለክታል።

በተጨማሪም ክፍለ ጦሩ፤ አስቸጋሪ በሆነ መልክዓ ምድር ውስጥ “የጠላትን የጥፋት መረብ በመስበር እና በመበጣጠስ” በኩል የነበረው ሚና የተጣለበትን ሀገራዊ ግዳጅ የመፈፀም አቅሙን ያረጋገጠበት ነው ብለዋል።

አዛዡ ይህ በውጤት የታጀበ ስምሪት ነው ያሉት ሲሆን የክፍለጦሩ ሠራዊት በአካልና በታክቲክ ከፍተኛ የብቃት ደረጃ  እንደደረሰ ያሳያል ሲሉ ተናግረዋል።

በተጨማሪም ኮሎኔሉ የክፍለጦሩ ሠራዊት  ዝግጁነት ባረጋገጠበት ወቅት የክፍለ ጦሩ “አስደማሚ ድልና ለአፍታም ቢሆን የማይላላው” ወታደራዊ ዝግጁነት አስተማማኝ የሀገር ደህንነት ዋስትና  አረጋግጠዋል ተብሏል።

ተጨማሪ ዜናዎችንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ይጎብኙ፦

YouTube ➲ t.ly/vSgS
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
Twitter ➲ t.ly/mxA
Telegram
Addis Maleda - አዲስ ማለዳ
ዜና ከምንጩ
❤15😁6👎2👍1
September 3, 2026 3.4K 2 2