ተጠርጣሪ ጋዜጠኛ ታደሠ ዳኛቸው የዋስትና መብቱ እንዲከበር ሊጠይቁ እንደሆነ ጠበቃቸው ለአዲስ ማለዳ ገለጹ
ረቡዕ፣ ነሐሴ 27 ቀን 2018 ዓ.ም (#አዲስ_ማለዳ)
የኤን.ቢ.ሲ ጋዜጠኛው ታደሠ ዳኛቸው ምክንያቱ በውል ባልታወቀ ጉዳይ እንደታሠረ አዲስ ማለዳ የጋዜጠኛውን ባለቤት አነጋግራ እንደዘገበች ይታወሳል ።
በዚሁ መሠረትም አዲስ ማለዳ የጋዜጠኛውን ጠበቃ ያነጋገረች ሲሆን ጠበቃው እንዳሉትም ጋዜጠኛው የታሠረበትም ምክንያት “ፍሬ አልባ ነው” ያሉ ሲሆን ሁነቱንም ሲገልፁት ግልፅ የሆነ ምክንያት የለም ብለዋል ።
ሆኖም ፖሊስ ጋዜጠኛውን በተመለከተ ምርመራ እያደረገ እንደሆነ እና ፍርድ ቤትም ለምርመራ ጊዜ 11 ቀናትን በመስጠት ለጳጉሜ 2 ቀን ቀጠሮ መሠጠቱን ጠበቃው ተናግረዋል ።
ፍርድ ቤቱ ቀጠሮ በሰጠበት ቀን ጋዜጠኛው ከእስር እንዲወጣ እና የዋስትና መብቱ እንዲጠበቅ ለማድረግ እንዳሰቡ ጠበቃ ሀይሉ ታደሠ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል ።
ጋዜጠኛ ታደሠ ዳኛቸው የታሠረው በጥርጣሬ ደረጃ እንጂ በግልፅ ይህ ነው የተባለ ነገር አለመኖሩንም ጭምር ጠበቃው ተናግረዋል ።
ሆኖም በጳጉሜ ሁለት የተቀጠረው ቀጠሮ ላይ ፖሊስ ምርመራውን ጨርሶ ውጤት ያቀርባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልፀዋል ።
ተጨማሪ ዜናዎችንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ይጎብኙ፦
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
Twitter ➲ t.ly/mxA
Telegram
Addis Maleda - አዲስ ማለዳ
ዜና ከምንጩ

4
2
1September 2, 2026 3.9K 3