የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ከአስር ዓመታት በኃላ በግብፅ የስራ ጉብኝት ማድረግ ጀመሩ ረቡዕ፣ ነሐሴ 27… — Addis Maleda - አዲስ ማለዳ — TG.ME

Addis Maleda - አዲስ ማለዳPhoto
የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ  ጂንፒንግ  ከአስር ዓመታት በኃላ በግብፅ የስራ ጉብኝት ማድረግ ጀመሩ

 ረቡዕ፣ ነሐሴ 27  ቀን 2018 ዓ.ም (#አዲስ_ማለዳ)
 
የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ  ለመጀመሪያ ጊዜ በትላንትናዉ ምሽት ከ10 ዓመታት በኃላ  በግብፅ  የሚያደርጉትን ይፋዊ ጉብኝት መጀመራቸዉ ተሰማ።

የግብፅ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አል-ሲሲ ዥን በካይሮ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቀባበል አድርገውላቸዋል ተብሏል። በተጨማሪም ሁለቱ መሪዎች የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን ለማጠናከር እና የሀገሮቹን አጠቃላይ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ተግባራዊ ለማድረግ እንዲሁም የጋራ ፍላጎት  ባላቸዉ ቀጠናዊና እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች እንደሚወያዩ ይጠበቃል።
 
የግብፅ ፕሬዝዳንት ቢሮ  በትናንትናዉ  ዕለት   እንደገለጸዉ ከሆነ ጉብኝቱ  እ.አ.አ  በ2014 በሁለቱ ሀገራት  መካከል  የተፈረመውን አጠቃላይ ስትራቴጂካዊ  አጋርነት ስምምነት ተግባራዊ ማድረግ ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ አስታውቋል።

እንደ ቢሮው  ገለጻ  ውይይቶቹ በቀጠናዊና እና ዓለም አቀፍ ለዉጦች ላይ ምክክሮችን እንደሚያክትቱ ታውቋል።

ፕሬዝዳንቱ በግብፅ መንግስታዊ ጋዜጦች አል-አህራም፣ አል-አክባር እና አል-ጉምሁሪያ በታተመ ጽሁፋቸው ላይ በቻይና እና በግብፅ መካከል ያለው ግንኙነት ከ70 ዓመታት ወዳጅነት በኋላ “በታሪክ ውስጥ በጣም ጥሩ ወቅት ላይ” መሆኑን ተናግረዋል።
 
ዢ የባህል ልውውጦችን ማጠናከር እና የቻይና-አረብ እና የቻይና-አፍሪካ ትብብርን የበለጠ ማጠናከር እንዳለበትም አሳስበዋል። ፕሬዝዳንቱ ለመጨረሻ ጊዜ  ግብፅን የጎበኙት እ.አ.አ ጥር 2016  ሲሆን ፕሬዝዳንት ከሆኑ በኋላ ወደ ሀገሪቱ ያደረጉት የመጀመሪያ ጉብኝት ነበር።

በዚያ ጉብኝት ወቅት ዢ ከአል-ሲሲ ጋር ተገናኝተው የሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት 60ኛ አመት ሥነ-ስርዓት ላይ መሳተፋቸው የሚታወስ ነው። አል-ሲሲ ብዙ ጊዜ ቻይናን የጎበኙ ሲሆን የመጨረሻ  ጉብኝታቸዉ  እ.አ.አ  በግንቦት 2024 ነበር።

ግብፅ እና ቻይና  እ.አ.አ በ1956 ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የመሰረቱ ሲሆን ይህም ግብፅ  የቻይናን ሪፐሊክነት እውቅና የሰጠች የመጀመሪያዋ የአረብ እና የአፍሪካ ሀገር አድርጓታል።

ቤጂንግ  እ.አ.አ በ1956 የሲውዝ ቀውስ ወቅት ለካይሮ ድጋፍ ያደረገች ሲሆን ግብፅ ደግሞ እ.አ.አ በ1971 ቻይና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት መቀመጫዋን እንድታስመልስ  ድጋፏን ችራለች።

ተጨማሪ ዜናዎችንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ይጎብኙ፦

YouTube ➲ t.ly/vSgS
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
Twitter ➲ t.ly/mxA
Telegram
Addis Maleda - አዲስ ማለዳ
ዜና ከምንጩ
❤9
September 2, 2026 2.6K 1