የአሜሪካ እና የኢራን ግጭት ዳግም አገርሽቶ ከባድ የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ ረቡዕ፣ ነሐሴ 27 ቀን 2018… — Addis Maleda - አዲስ ማለዳ — TG.ME

Addis Maleda - አዲስ ማለዳPhoto
የአሜሪካ እና የኢራን ግጭት ዳግም አገርሽቶ ከባድ የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ረቡዕ፣ ነሐሴ 27  ቀን 2018 ዓ.ም (#አዲስ_ማለዳ)

የአሜሪካ እና የኢራን ግጭት ከአንድ ወር ወታደራዊ ውጥረት በኋላ ዳግም አገርሽቶ ምሽቱን  ከባድ የተኩስ ልውውጥ እና አዳዲስ ጥቃቶች በመፈጸሙ ምክንያት ዳግም መባባሱ ተገለፀ።

የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ፤ የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ፣ ወታደራዊ ይዞታዎችን እንዲሁም ሆርሙዝ አካባቢ የሚገኙ የአየር መከላከያ ስርዓቶችን እና የሚሳኤል ማስወንጨፊያዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት መፈጸሙን አስታውቋል።

አሜሪካ ይህን ጥቃት የፈጸመችው፤ ኢራን፣ በዓለም አቀፍ የንግድ መርከቦች እና በባህር ላይ ስጋት ደግናለች በሚል ምክንያት እንደሆነ ገልጻለች።

ኢራን ለአሜሪካ ጥቃት ምላሽ ለመስጠት ሚሳኤሎችን እና ሰው የጦር አውሮፕላኖችን(ድሮን) በመጠቀም በመካከለኛው ምስራቅ በሚገኙ የአሜሪካ የጦር አምባዎች ላይ ጥቃት አድርሳለች።

የኢራን ወታደራዊ ኃይሎች ለአሜሪካ ድርጊት "አደገኛ እና አጥፊ ምላሽ" መስጠታቸውን ገልጸዋል።

የኢራን መንግስት መገናኛ ብዙኃን የአሜሪካ ጥቃቶች በደቡባዊ ኢራን በሚገኙ መሰረተ ልማቶች ላይ ማረፋቸውንና የሰዎች ህይወት ማለፉን የዘገቡ ሲሆን፣ በአንጻሩ የአሜሪካ ወታደራዊ ክንፍ ጥቃቱ በወታደራዊ ኢላማዎች ላይ ብቻ ያተኮረ ነው በማለት ምላሽ ሰጥቷል።

አሜሪካ፤ ኢራን፣ ተጨማሪ ምላሽ የምትሰጥ ከሆነ አደገኛ ጥቃት ይጠብቃታል ስትል የዛተች ሲሆን ቀጣናው ዳግም ወደ ሙሉ ጦርነት ሊያመራ ይችላል የሚለው ስጋት ደግሞ በዓለም አቀፍ ደረጃ ማየሉን ሮይተርስ ዘግቧል።
 
የኢራኑ ፕሬዝዳን መስዑድ ፔዝሼኪያን፤ ኪርጊክስታን የሚገኙ ሲሆን በጦርነቱ ዙሪያ ከቻይና፣ ሩሲያ፣ ቱርክ እና ህንድ እንዲሁም ከሌሎች መሪዎች ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ተጨማሪ ዜናዎችንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ይጎብኙ፦

YouTube ➲ t.ly/vSgS
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
Twitter ➲ t.ly/mxA
Telegram
Addis Maleda - አዲስ ማለዳ
ዜና ከምንጩ
❤6
September 2, 2026 2.2K 3