ሩሲያ ወደ ውጭ የምትልከው ነዳጅ እስከ መስከረም መጨረሻ ታግዶ እንዲቆይ ወሰነች ቅዳሜ፣ ነሐሴ 23 ቀን… — Addis Maleda - አዲስ ማለዳ — TG.ME

Addis Maleda - አዲስ ማለዳPhoto
ሩሲያ ወደ ውጭ የምትልከው ነዳጅ እስከ መስከረም መጨረሻ ታግዶ እንዲቆይ ወሰነች

ቅዳሜ፣ ነሐሴ 23 ቀን 2018 ዓ.ም (#አዲስ_ማለዳ)

ሩሲያ የአገር ውስጥ የነዳጅ ገበያን ለማረጋጋት በሚል ወደ ውጭ በምትልከው ነዳጅ ላይ የጣለችው እገዳ  እ.አ.አ መስከረም 30 ቀን 2026 ድረስ ማራዘሟን ዛሬ ቅዳሜ ይፋ አደረገች።

የአውሮፓን ህብረት ፕሬዝዳንት በቅርቡ ከሩሲያ የሚገባው ነዳጅ መቅረቱ፣ አህጉሩን ከባድ ዋጋ እያስከፈለው መሆኑን ተናግረው ነበር።

የሩሲያ መንግሥት ይህንን አስመልክቶ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ፤ የእገዳ ውሳኔው ለከባድ ተሽከርካሪዎች የሚውለው ዲዝል በተጨማሪ የማሪን ነዳጅ እና የጋዝ ምርቶችን በሙሉ  ያካትታል።

ውሳኔውን በተመለከተ በሰጠው ማብራሪያም “እርምጃው የተወሰደው የአገር ውስጥ የነዳጅ ገበያን ለማረጋጋት እና የዋጋ ንረትን ለመግታት ታስቦ ነው” ብሏል።

ሮይተርስ ኢንዱስትሪ ላይ የሚሰሩ ምንጮችን እማኝ አድርጎ እንደዘገበው፤ ሩሲያ እገዳውን እንድታራዝም ያስገደዳት በዩክሬን ድሮን  በሚደርሱ ጥቃቶች ምክንያት በርካታ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካዎቿ አገልግሎት ማቋረጣቸውን ተከተሎ በአገር ውስጥ የታየውን የነዳጅ እጥረት ለመቅረፍ በማለም ነው።

ሩሲያ ከዚህ ውሳኔዋ አስቀድሞ ወደውጵ በሚላከው ነዳጅ ላይ፣ በአውሮፓውያኑ  ከሐምሌ አንድ እስከ ሐምሌ 25 ባለው ጊዜ ውስጥ እገዳ ጥላ የነበረ ቢሆንም እስከ ነሐሴ 25 ቀን አራዝማው ነበር። አሁን ደግሞ እገዳው ለተጨማሪ አንድ ወር እንዲራዘም ወስናለች።

ከዚህ በተጨማሪም ሩሲያ አምራች ባልሆኑ ኩባንያዎች የሚደረግ የዲዝል እና የሞተር ቤንዚን እስከ ጥር  2027 እንዲሁም የጄት ነዳጅ 2026  ድረስ ታግዶ እንዲቆይ ማድረጓ የሚታወስ ነው።

ከአሜሪካ ቀጥሎ በዓለም ሁለተኛዋ ትልቋ የዲዝል ላኪ የሆነችው ሩሲያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሚሳኤል እና በድሮን ጥቃቶች ሳቢያ የማጣሪያ አቅሟ በመቀነሱ ምክንያት ወደ ውጭ የምትልከው የነዳጅ መጠን በከፍተኛ ሁኔታ እየቀነሰ ነው ተብሏል።


ተጨማሪ ዜናዎችንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ይጎብኙ፦

YouTube ➲ t.ly/vSgS
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
Twitter ➲ t.ly/mxA
Telegram
Addis Maleda - አዲስ ማለዳ
ዜና ከምንጩ
❤13🤔2👍1😱1🙏1
August 29, 2026 5.2K 1 4