የኢሕአፓ አመራርና አባል ተጨማሪ ምስክር እንዲያቀርቡ ለቀጣይ ሳምንት ሐሙስ ቀጠሮ ተሰጣቸው ዓርብ፣ ነሐሴ 22… — Addis Maleda - አዲስ ማለዳ — TG.ME

Addis Maleda - አዲስ ማለዳPhoto
የኢሕአፓ አመራርና አባል ተጨማሪ ምስክር እንዲያቀርቡ ለቀጣይ ሳምንት ሐሙስ ቀጠሮ ተሰጣቸው

ዓርብ፣ ነሐሴ 22 ቀን 2018 ዓ.ም (#አዲስ_ማለዳ)

ተጠርጣሪዎቹ ተጨማሪ ምስክር እንዲያቀርቡ በማለት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለነሐሴ  28 ቀጠሮ መስጠቱን ጠበቃቸው ሰለሞን ገዛኸኝ ለአዲስ ማለዳ ተናገሩ።

በሽብር ወንጀል የተጠረጠሩት፤ የኢሕአፓ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው  ይስሐቅ ወልዳይ፣ የፓርቲው አባል አበበ አካሉ እንዲሁም ጠበቃ አበራ ንጉሥ በዛሬው ዕለት  በከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበው እንደነበር ጠበቃቸው ሰለሞን ገዛኸኝ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

የከፍተኛ  ፍርድ ቤት ዛሬ ባስቻለው ችሎት ተከሳሾቹ  የፌደራል ፖሊስ የምርመራ መዝገቡን ማጠናቀቁን እና የቴክኒክና የፎረንሲክ መረጃዎች በቂ ስለሆኑ የፌደራል ፖሊስም መረጃዎችን ወደ ማጠናቀቁ  እንደደረሠ አሰረድቷል።

ነገር ግን ተከሳሾቹ ያቀረቧቸው ምስክሮች በቁጥር ሁለት ብቻ  በመሆናቸው ፍርድ ቤቱ ለመጨረሻ ጊዜ በሚል ለቀጣይ ሳምንት ሐሙስ ነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ቀጠሮ እንደተሠጣቸው ጠበቃ ሰለሞን አስረድተዋል።

ተጨማሪ ዜናዎችንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ይጎብኙ፦

YouTube ➲ t.ly/vSgS
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
Twitter ➲ t.ly/mxA
Telegram
Addis Maleda - አዲስ ማለዳ
ዜና ከምንጩ
❤14😢4👎1🥰1
August 28, 2026 6.6K 1 5