በኔፓል የጎርፍ አደጋ ከ540 በላይ ሰዎችን ህይወት ቀጥፎ ተጨማሪ የጎርፍ ሥጋት መደቀኑ ተሰማ
ዓርብ፣ ነሐሴ 22 ቀን 2018 ዓ.ም (#አዲስ_ማለዳ)
በኔፓል እና በቻይና ድንበር ቲቤት ላይ በተከሰተው ከፍተኛ እና ድንገተኛ የጎርፍ አደጋ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ቢያንስ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ 547 ደረሰ፡፡ ከሞቱት በተጨማሪ፤ ከአንድ ሺህ ሰዎች በላይ የጠፉ ሲሆን የነፍስ አድን ቡድኖች በጭቃና ፍርስራሽ የተሸፈኑ ቦታዎችን መቆፈራቸውን የቀጠሉ ቢሆንም በቻይና በኩል ነፍስ አድኖቹ ደህንነቱ ወደተጠበቀ ቦታ እንዲሄዱ አሳሰባለች።
ረቡዕ ዕለት በሂማላያ ተራራማ አካባቢ በተከሰተ ከፍተኛ የበረዶ ግግር ተደርምሶ የተነሳው የጎርፍ እና ጭቃ ጎርፍ፣ በወንዞች መስመር ላይ ያሉ መንደሮችን፣ የውሃና ኤሌክትሪክ ማመንጫዎችን እና የመሰረተ ልማት አውታሮችን ከጥቅም ውጪ አድርጓቸዋል፡፡
ቻይና አሉ የሚባሉ መሃንዲሶቿ በቡድን ሁነው ጎርፉን መቋቋም የሚችል ንድፍ (3ዲ) ሰርተው፤ ግንባታ እንዲጀመር አሳስባለች። ይህ ቡድን በከፍተኛ አመራሮች የሚመራም ይሆናል ተብሏል።
የኔፓል ባለሥልጣናት የሟቾች ቁጥር ከ500 በላይ እንደሚደርስ የገለጹ ሲሆን በከ1,000 በላይ ሰዎች የት እንደደረሱ አልታወቀም። በርካታ የውጭ ሀገር ቱሪስቶችም ከእነርሱ ውስጥ ይገኙበታል፡፡
በአደጋው ምክንያት በተፈጠሩ የመሬት መንሸራተት ሳቢያ ወንዞች ተዘጋግተው የተፈጠሩ ሰው ሰራሽ ሐይቆች የሞሉ ሲሆን የመፍሰስ አደጋ በመደቀናቸው አዲስ የጎርፍ ማዕበል እንዳይከሰት ስጋት ፈጥሯል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
በሌላ በኩል ደግሞ ለሦስት ሰዓት ያህል ፍለጋው ቁሞ የነበረ ሲሆን የቻይና ባለስልጣናት በቲቤት በኩል የሚገኙ የነፍስ አድን ቡድኖችን ጊዜያዊ ደኀንነቱ ወደተጠበቀ ቦታ እንዲያፈገፍጉ ትዛዝ አስተላልፈዋል።
የኔፓል ጦር እና ፖሊስ፤ ሄሊኮፕተሮችን እና ከባድ ማሽነሪዎችን በመጠቀም የተዘጋጉ መንገዶችን ለመክፈት እና ሰዎችን ለማዳን እየሰሩ ነው። በተለይም በ'ትሪሹሊ በተሰኘች የውሃ ኤሌክትሪክ ማመንጫ ዋሻ ውስጥ ተቀርቅረው የነበሩ ከ300 በላይ ሰራተኞችን ማዳን የተቻለ ሲሆን የቀሩትን የማውጣት ስራ በከፍተኛ ጥንቃቄ ቀጥሏል።
ህንድ እና ቻይና የድንበር አካባቢዎቻቸውን በከፍተኛ ጥንቃቄ ላይ ያደረጉ ሲሆን፣ ህንድ በጋንዳክ ወንዝ ተፋሰስ አቅራቢያ የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቿን ከቀያቸው እያስወጣች ነው።
ተጨማሪ ዜናዎችንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ይጎብኙ፦
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
Twitter ➲ t.ly/mxA
Telegram
Addis Maleda - አዲስ ማለዳ
ዜና ከምንጩ

10
3August 28, 2026 4.8K 4