የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በማዕድን ዘርፍ የሚስተዋሉ ህገ-ወጥ የማዕድን ግብይቶችና የአደገኛ ኬሚካሎች አጠቃቀም ፈተና ሆነዋል ሲል ገለጸ
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም (#አዲስ_ማለዳ)
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በማዕድን ዘርፍ የሚስተዋሉ ህገ-ወጥ የማዕድን ግብይቶችና የአደገኛ ኬሚካሎች አጠቃቀም ተግዳሮቶች መሆናቸውን አስታወቀ። ቤንሻንጉል ክልል በኢትዮጵያ የወርቅ ምርት ከሚመርትባቸው ቦታውች ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ አለው።
ክልሉ ይህን ያለው በትናንትናው ዕለት “የማዕድን ሀብታችን ለዘላቂ ብልፅግናችን” በሚል መሪ ሐሳብ የማዕድን ዘርፉን ምርታማነት ከማሳደግ ባለፈ፣ በዘርፉ የሚስተዋሉ ማነቆዎችን ለመፍታትን ማዕከል ያደረገ መድረክ በአሶሳ ከተማ ሲካሄድ፤ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን በዘርፉ የሚታዩ ህገ-ወጥ ተግባራትን ለመከላከልና ሀገርን ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታትና ከዘርፉ የሚገኘውን ሀገራዊ ጥቅም ለማሳደግ የተቀናጀ አሠራርና የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ቁርጠኝነት የሚጠይቅ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
በክልሉ የሚገኙ የወርቅ አምራች ፋብሪካዎች ዘርፉን ለማጠናከር ትልቅ አቅም እየሆኑ መምጣታቸውን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ እንደ ሀገርና እንደ ክልል የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል የንቅናቄው ፋይዳ የጎላ መሆኑን አስረድተዋል።
የክልሉ ማዕድን ቢሮ ኃላፊ ቲጃኒ አደም በበኩላቸው፤ በበጀት ዓመቱ 8 ሺህ 985 ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ መላኩን ገልጸዋል። ቢሮው ከወርቅ ምርት በተጨማሪ የከሰል ድንጋይና የእምነበረድ ምርትን ወደ ከፍተኛ ደረጃ ለማሸጋገርና የኢንዱስትሪ ግብዓቶችን ለማሳደግ በትኩረት እየሠራ መሆኑን ጠቁመዋል ሲል የክልሉ ኮሚኒኬሽን ያጋራው መረጃ ያመለክታል።
ተጨማሪ ዜናዎችንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ይጎብኙ፦
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
Twitter ➲ t.ly/mxA
Telegram
Addis Maleda - አዲስ ማለዳ
ዜና ከምንጩ

4September 1, 2026 2.8K 8