የአሜሪካ የጦር ኃይል ጸኃፊ ከሚኒስትሩ ጋር በመጣላታቸው ምክንያት ለትራምፕ የሥራ የመልቀቂያ ደብዳቤያቸውን አስገቡ
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም (#አዲስ_ማለዳ)
የአሜሪካ የጦር ኃይል ጸኃፊ ዳንኤል ድሪስኮል ከሀገሪቱ የመከላከያ ሚኒስትር ዋና ጸኃፊ ፒት ሄግዝ ጋር ለወራት የዘለቀ አለመግባባት ከተፈጠረ በኋላ ለፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሥራ መልቀቂያቸውን ማቅረባቸው ተገለጸ።
ዳንኤል ለአሜሪካ ጦር ከፍተኛ የሲቪል መሪው እንደሆኑም የተገለጸ ሲሆን መልቀቃቸው የሚጠበቅ ቢሆንም፣ ጦሩ በተለያዩ ጉዳዮች ውጥረት ላይ በሆነበት ወቅት ላይ ነው ተብሏል።
በተጨማሪም ኢራን ላይ የሚወሰደው እርምጃ በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ አሜሪካን በበቂ ሁኔታ ላንጠብቃት እንችላለን፤ ማለትም አሁን ላይ ባላቸው አቋም በሚል ፍርቻ ከፍተኛ የመከላከያ ወታደራዊ አመራሮች ለሄግዝ ማስጠንቀቂያ መስጠታቸውም በዚሁ ሰሞን መዘገቡ ይታወሳል።
ዳንኤል ድሪስኮል ከመከላከያ ሚኒስትሩ ፒት ሄግሴዝ ጋር በጦር ኃይሉ ማሻሻያዎች እና የከፍተኛ ጄኔራሎች ከኃላፊነት መነሳት እና መባረር እንዲሁም ዘመናዊ የሆኑ ሰው አልባ አውሮፕላኖች (ድሮን) ቴክኖሎጂ ፕሮግራሞች ትግበራ ዙሪያ ጠንካራ አለመግባባቶች እንደነበሯቸው ተነግሯል።
የነጩ ቤተመንግሥት ቃል አቀባይ እንዳስታወቁት ከሆነ ደግሞ፤ ዳንኤል የትራምፕን አጀንዳ በማስፈጸም፣ የጦር ኃይሉን ዝግጁነት በማሳደግ እና በሩሲያ-ዩክሬን የሰላም ድርድር ሂደት ላይ ባደረጉት አስተዋጽኦ ከፍተኛ አፈጻጸም እንደነበራቸው መስክረዋል።
ይህ የሥራ መልቀቂያ፤ በቅርቡ በመከላከያ ሚኒስትሩ እየተወሰዱ ካሉ በርካታ የከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ከኃላፊነት ማንሳት እና የባህር ኃይል ጸኃፊ ላይ ያለው የስብጥር ለውጥ እና ስንብቶች እየበዙ ከመጡ በኋላ መሆኑን ኒውዮርክ ታይምስ ዘግቧል።
ተጨማሪ ዜናዎችንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ይጎብኙ፦
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
Twitter ➲ t.ly/mxA
Telegram
Addis Maleda - አዲስ ማለዳ
ዜና ከምንጩ

7September 1, 2026 3K 6