ደቡብ ኮሪያ የአሜሪካ እና የሰሜን ኮሪያን የኒውክሌር ድርድር እና ዲፕሎማሲያዊ ውይይት ለመጀመር የሚደረገውን… — Addis Maleda - አዲስ ማለዳ — TG.ME

Addis Maleda - አዲስ ማለዳPhoto
ደቡብ ኮሪያ የአሜሪካ እና የሰሜን ኮሪያን የኒውክሌር ድርድር እና ዲፕሎማሲያዊ ውይይት ለመጀመር የሚደረገውን ጥረት እንደምትደግፍ ገለጸች

ዓርብ፣ ነሐሴ 22 ቀን 2018 ዓ.ም (#አዲስ_ማለዳ)

ደቡብ ኮሪያ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ ከሰሜን ኮሪያ ጋር ተቋርጦ የቆየውን ውይይት እንደገና ለማስጀመር የሚያደርጉትን ጥረት በመደገፍ፣ ሁለቱ ወገኖች ለሚያካሂዱት ንግግር አስፈላጊውን ድጋፍ ትሰጣለች ሲል የሀገሪቱ የብሔራዊ ደኀንነት ገለጸ።

የብሔራዊ ደኀንነት አማካሪው ዊ ሱንግ ላክ ግንኙነቱን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡ ሲሆን፣ በዋሽንግተን እና በፒዮንግያንግ መካከል የሚደረገው ውይይት እንደገና መመለስ  በሰሜን ኮሪያ የኒውክለር መሳሪያዎች  ጉዳይ ላይ ተጨባጭ እና ጥርት ያለ እድገት በማምጣት ላይ ማተኮር እንዳለበት አሳስበዋል።

እንደ ሮይተርስ ዘገባ ከሆነ አማካሪው የአሜሪካ እና የሰሜን ኮሪያ የኒውክሌር ውይይት ዳግም መጀመር፣ የደቡብ ኮሪያን የደህንነት ዝግጁነት በማያዳክምበት ሁኔታ ላይ ተመርኩዞ መከናወን እንደሌለበትና ሴኡል ከሂደቱ ውጭ እንዳትሆን ጥንቃቄ እንደሚደረግ ገልጸዋል።

ይህ አዲሱ የደቡብ ኮሪያ አቋም የተሰማው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ ኡን ጋር በኒውክሌር  መርሃ ግብር እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ዙሪያ ለመወያየት ባላቸው ፍላጎት የተነሳ ከደቡብ ኮሪያ ጋር የሚደረጉ የጋራ ወታደራዊ ልምምዶችን ለመቀነስ መወሰናቸውን ተከትሎ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ ከጃፓን እና ከአሜሪካ ጋር በመሆን መስከረም ሁለተኛው ሳምንት ላይ የሰሜን ኮሪያን የሚሳኤል እና የኒውክለር ዛቻ ለመቀነስ በሚል ወታደራዊ ልምምድ እንደሚያካሂዱ ሴኡል አስታውቃለች፡፡

ተጨማሪ ዜናዎችንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ይጎብኙ፦

YouTube ➲ t.ly/vSgS
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
Twitter ➲ t.ly/mxA
Telegram
Addis Maleda - አዲስ ማለዳ
ዜና ከምንጩ
❤5👍1
August 28, 2026 4.4K